እንዲህም አሉ፦ “ኑ አንድ ከተማ እንመሥርት፤ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ እንዳንበታተን ስማችንን እናስጠራ።”
2 ሳሙኤል 8:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት የጨው ሸለቆ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ዐሥራ ስምንት ሺህ ኤዶማውያንን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ ዝነኛ ሆነ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ኤዶማውያንን ገድሎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ዐሥራ ስምንት ሺህ ኤዶማውያንን ገድሎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በተመለሰ ጊዜ ከኤዶምያስ ዐሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች በጨው ሸለቆ ውስጥ በመምታቱ ስሙ ተጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በተመለሰ ጊዜ ከኤዶምያስ አሥራ ስምንት ሺህ ሰዎች በጨው ሸለቆ ውስጥ በመምታቱ ስሙ ተጠራ። |
እንዲህም አሉ፦ “ኑ አንድ ከተማ እንመሥርት፤ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ እንዳንበታተን ስማችንን እናስጠራ።”
በሄድክበት ስፍራ ሁሉ እኔ ከአንተ ጋር ነበርኩ፤ ወደፊትም በተራመድህ መጠን ጠላቶችህን ድል አደረግሁልህ፤ ገና ደግሞ በዓለም እንደ ታወቁት ታላላቅ መሪዎች ዝነኛ አደርግሃለሁ።
አሜስያስ “የጨው ሸለቆ” እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ዐሥር ሺህ የሚሆኑ የኤዶም ወታደሮችን ፈጀ፤ ሴላዕ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ይዞ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት፤ እስከ አሁንም በዚሁ ስም ትጠራለች።
ከዚህ በኋላ አሜስያስ በወኔ ተነሣሥቶ ወታደሮቹን በመምራት ወደ ጨው ሸለቆ ሄደ፤ በዚያም ወታደሮቹ በኤዶም ሠራዊት ላይ አደጋ ጥለው ዐሥር ሺህ ወታደሮችን ገደሉ፤