በመላ አገሪቱም ሕዝቡ እርስ በርስ መጣላት ጀመረ፤ እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፦ “ንጉሥ ዳዊት ከጠላቶቻችን እጅ አድኖናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አውጥቶናል፤ አሁን ግን ከአቤሴሎም ፊት በመሸሽ አገሪቱን ትቶ ሄዶአል።
2 ሳሙኤል 5:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊት ወደ ባዓል ፈራጺም ወርዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል ካደረገ በኋላ “እግዚአብሔር በጠላቶቼ መካከል እንደ ጐርፍ ሰባብሮ ገባ” አለ፤ ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም “ባዓል ፈራጺም” ተብሎ ተጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ዳዊት ወደ በኣልፐራሲም ሄዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው። እርሱም “የጐርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ፣ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በፊቴ አፈራረሳቸው” አለ። ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም “በኣልፐራሲም” ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ዳዊት ወደ ባዓል ፈራጺም ሄዶ ፍልስጥኤማውያንን ድል አደረጋቸው። እርሱም “የጐርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ፥ ጌታም ጠላቶቼን በፊቴ አፈራረሳቸው” አለ። በዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም ባዓል ፈራጺም ተባለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከላይኛው መጋደያ መጣ፤ በዚያም መታቸውና፥ “ውኃ እንደሚያጠፋ እግዚአብሔር ጠላቶቼን ፍልስጥኤማውያንን በፊቴ አጠፋቸው” አለ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም “የላይኛው መጋደያ” ተብሎ ተጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደ በኣልፐራሲም መጣ፥ በዚያም መታቸውና፦ ውኃ እንዲያፈርስ እግዚአብሔር ጠላቶቼን በፊቴ አፈረሳቸው አለ። ስለዚህም የዚያን ስፍራ ስም በኣልፐራሲም ብሎ ጠራው። |
በመላ አገሪቱም ሕዝቡ እርስ በርስ መጣላት ጀመረ፤ እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፦ “ንጉሥ ዳዊት ከጠላቶቻችን እጅ አድኖናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አውጥቶናል፤ አሁን ግን ከአቤሴሎም ፊት በመሸሽ አገሪቱን ትቶ ሄዶአል።
ስለዚህ ዳዊት ባዓልፈራጺም ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጥሎ ድል ካደረጋቸው በኋላ “የጠላትን ሠራዊት እንደ ጐርፍ ጥሼ እንዳልፍ እግዚአብሔር ረዳኝ” አለ፤ ከዚያም በኋላ ያ ስፍራ “ባዓልፈራጺም” ተብሎ ተጠራ፤
እግዚአብሔር በጰራጺም ተራራ ላይና በገባዖን ሸለቆ ላይ እንዳደረገው፥ አሁንም ያልተለመደ ሥራውን ለመሥራትና ለሰው እንግዳ የሆነው ተግባሩን ለመፈጸም ይነሣል።
ሕዝብህን ለመታደግ፥ ቀብተህ ያነገሥከውንም ንጉሥ ለማዳን ወጣህ፤ የጥፋት አገር መሪ የሆነውን ቀጠቀጥከው፤ ተከታዮቹንም አጥፍተህ እርቃኑን አስቀረኸው። ከእግር እስከ ራሱም አራቈትከው።