እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል በርትተን እንዋጋ! እንግዲህ ሁሉ ነገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!”
2 ሳሙኤል 24:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብ ግን “ንጉሥ ሆይ! አምላክህ እግዚአብሔር የእስራኤል ሕዝብ አሁን ካሉት ይልቅ በመቶ እጅ ያብዛልህ፤ ይህንንም ሲያደርግ ለማየት እንድትበቃ ዕድሜህን ያርዝምልህ፤ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! ይህን ለማድረግ ስለምን ፈለግኽ?” አለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብ ግን ንጉሡን፣ “አምላክህ እግዚአብሔር ሰራዊቱን በመቶ ዕጥፍ ያብዛው፤ የጌታዬ የንጉሡ ዐይን ይህን ለማየት ይብቃ፤ ንጉሡ ጌታዬ ግን ይህን ለማድረግ የፈለገው ለምንድን ነው?” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብ ግን ንጉሡን፥ “ጌታ አምላክህ ሕዝቡን መቶ ዕጥፍ ያድርገው፤ የጌታዬ የንጉሡ ዐይን ይህን ለማየት ያብቃው፤ ንጉሡ ጌታዬ ግን ይህን ለማድረግ የፈለገው ለምንድን ነው?” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ንጉሡን፥ “የጌታዬ የንጉሡ ዐይን እያየ አምላክህ እግዚአብሔር ዛሬ ካለው ሕዝብ መጠን በላይ መቶ እጥፍ ይጨምርበት፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን ይህን ነገር ለምን ይፈልጋል?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ንጉሡን፦ የጌታዬ የንጉሡ ዓይን እያየ አምላክህ እግዚአብሔር ዛሬ ካለው ሕዝብ መጠን በላይ መቶ እጥፍ ይጨምርበት፥ ጌታዬ ንጉሡ ግን ይህን ነገር ለምን ይወድዳል? አለው። |
እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል በርትተን እንዋጋ! እንግዲህ ሁሉ ነገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!”
ይህንንም አይተሽ ፈገግታሽ በደስታ ይፈካል፤ ከባሕር የሚገኘው በረከትና፥ ከሕዝቦች የሚመጣው ሀብት የአንቺ ስለሚሆን፥ ከደስታሽ ብዛት የተነሣ ልብሽ ይፈነድቃል።