2 ሳሙኤል 23:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሠላሳዎቹ መካከል እጅግ ታዋቂ ቢሆንም በዝነኛነቱ ከሦስቱ ኀያላን ደረጃ አልደረሰም፤ ዳዊትም በናያን የክብር ዘቡ አዛዥ አድርጎ ሾሞት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሠላሳዎቹ ሁሉ በላይ የከበረ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ከሦስቱ እንደ አንዱ አልነበረም። ዳዊትም የክብር ዘበኞቹ አለቃ አድርጎ ሾመው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሠላሳዎቹ ይልቅ የከበረ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ከሦስቱ እንደ አንዱ አልነበረም። ዳዊትም የክብር ዘበኞቹ አለቃ አድርጎ ሾመው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሦስቱም ይልቅ የከበረ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ ሦስቱ አልደረሰም። ዳዊትም ትእዛዝ አስከባሪ አድርጎ ሾመው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሠላሳውም ይልቅ የከበረ ነበረ፥ ነገር ግን ወደ ሦስቱ አልደረሰም። ዳዊትም በክብር ዘበኞቹ ላይ ሾመው። |
ከሠላሳዎቹ መካከል የሌሎቹ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮአብ ወንድም ዐሣሄል፤ የቤተልሔሙ ተወላጅ የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፤ የሐሮድ ተወላጆች የሆኑት ሻማና ኤሊቃ፤ የፌሌጥ ተወላጅ የሆነው ሔሌጽ፤ የተቆዓ ተወላጅ የሆነው የዒቄሽ ልጅ ዒራ፤ የዐናቶት ተወላጅ የሆነው አቢዔዜር፤ የሑሻ ተወላጅ የሆነው መቡናይ፤ የአሖሕ ተወላጅ የሆነው ጻልሞን፤ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው ማህራይ፤ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው የባዕና ልጅ ሔሌብ፤ በብንያም ግዛት የምትገኘው የጊብዓ ተወላጅ የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፤ የፒርዓቶን ተወላጅ የሆነው በናያ፤ በጋዓሽ ሸለቆ አጠገብ የተወለደው ሂዳይ፤ የዓርባ ተወላጅ የሆነው ኢቢዓልቦን፤ የባርሑም ተወላጅ የሆነው ዓዝማዌት፤ የሻዓልቦን ተወላጅ የሆነው ኤልያሕባ፤ የያሼን ልጆች፤ ዮናትን፤ የሐራር ተወላጅ የሆነው ሻማ፤ የሐራር ተወላጅ የሆነው የሻራር ልጅ አሒአም፤ የማዕካ ተወላጅ የሆነው የአሐሰባይ ልጅ ኤሊፌሌጥ፤ የጊሎ ተወላጅ የሆነው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊዓም፤ የቀርሜሎስ ተወላጅ የሆነው ሔጽሮ፤ የዐረብ ተወላጅ የሆነው ፓዓራይ፤ የጾባ ልጅ የሆነው የናታን ልጅ ዪግአል የጋድ ተወላጅ የሆነው ባኒ፤ የዐሞን ተወላጅ የሆነው ጼሌቅ፤ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ የነበረውና የበኤሮት ተወላጅ የሆነው ናሕራይ፤ የያቲር ተወላጆች የሆኑት ዒራና ጋሬብ፤ ሒታዊው ኦርዮን። ዝነኞች የሆኑት ኀያላን ወታደሮች ጠቅላላ ድምር ሠላሳ ሰባት ነበር።
አቤሜሌክም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ዳዊት ለአንተ የታመነ የጦር መኰንን ነው፤ የአንተው የራስህ ዐማች ከመሆኑም ሌላ የክብር ዘብህ አዛዥ ነው፤ በቤተ መንግሥትህም አደባባይ እንደ እርሱ የሚከበር ማን አለ?