2 ሳሙኤል 22:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳግመኛ እንዳይነሡ አድርጌ እመታቸዋለሁ፤ በእግሬም ሥር ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ ተመልሰውም መቆም አልቻሉም፤ ከእግሬም ሥር ወድቀዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈጽሜ አጠፋኋቸው፤ አስጨነቅኻቸው ተመልሰውም እንዳይቆሙ፥ ከእግሬም ሥር ወድቀዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እቀጠቅጣቸዋለሁ፤ መቆምም አይችሉም፤ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ። |
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።
ወደ ኢያሱም አመጡአቸው፤ ኢያሱም የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ወደ እርሱ ጠራ፤ ከእርሱ ጋር የዘመቱት የጦር መኰንኖችም መጥተው እግራቸውን በነገሥታቱ አንገት ላይ እንዲያደርጉ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም እንደ ታዘዙት አደረጉ።