ሦስት ኪሎ ተኩል የሚመዝን ከነሐስ የተሠራ ጦር የያዘና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ዩሽቢበኖብ ተብሎ የሚጠራ አንድ ኀያል ሰው ዳዊትን ለመግደል አስቦ ነበር፤
2 ሳሙኤል 21:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤላውያን መካከል የተደረገ ሌላም ጦርነት ነበር፤ ስለዚህም ዳዊትና ተከታዮቹ ዘምተው ፍልስጥኤማውያንን ወጉ፤ ከውጊያዎቹም በአንዱ ዳዊት ደክሞት ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገና በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤል መካከል ጦርነት ተደረገ። ዳዊትም ከሰዎቹ ጋራ ሆኖ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወረደ፤ በዚያም ደከመው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደገና በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤል መካከል ጦርነት ተደረገ። ዳዊትም ከሰዎቹ ጋር ሆኖ ፍልስጥኤማውያንን ለመውጋት ወረደ፤ ዳዊትም ደከመው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤልም መካከል ደግሞ ጦርነት ሆነ፤ ዳዊትም፥ ከእርሱም ጋር አገልጋዮቹ ወረዱ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ተዋጉ፤ ዳዊትም ደከመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፍልስጥኤማውያንና በእስራኤልም መካከል ደግሞ ሰልፍ ነበረ፥ ዳዊትም ከእርሱም ጋር ባሪያዎቹ ወረዱ፥ ከፍልስጥኤማውያንም ጋር ተዋጉ፥ ዳዊትም ደከመ። |
ሦስት ኪሎ ተኩል የሚመዝን ከነሐስ የተሠራ ጦር የያዘና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ዩሽቢበኖብ ተብሎ የሚጠራ አንድ ኀያል ሰው ዳዊትን ለመግደል አስቦ ነበር፤
ዳዊት በእስራኤል ላይ መንገሡን ፍልስጥኤማውያን ሰሙ፤ ስለዚህም ሠራዊታቸው ዳዊትን ለመማረክ ገሥግሦ ሄደ፤ ዳዊት የእነርሱን መምጣት በሰማ ጊዜ ወደ ተመሸገ ስፍራ ወረደ፤
ጥቂት ዘግየት ብሎም ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ድል አድርጎ በቊጥጥሩ ሥር አደረጋቸው፤ “ሜቴግ አማ” የተባለችውንም ከተማ ከእነርሱ እጅ ወሰደ።
ዘግየት ብሎም በጌዜር የሚኖሩ ፍልስጥኤማውያን ላይ ጦርነት ተደረገ፤ በዚያን ጊዜ የሑሻ ተወላጅ የሆነው ሲበካይ፥ ከራፋይም ወገን የነበረውን ሲፓይ ተብሎ የሚጠራውን ኀያል ሰው ገደለ፤ ፍልስጥኤማውያንም ተሸነፉ።
የምትተማመንባቸው ክንዶችህ ይንቀጠቀጣሉ፤ አሁን ብርቱ የሆኑ እግሮችህ ይዝላሉ፤ ጥርሶችህ ቊጥራቸው ከማነሳቸው የተነሣ ምግብ ማኘክ አይችሉም፤ ዐይኖችህ ከመፍዘዛቸው የተነሣ አጥርተው ማየት ይሳናቸዋል።