ከዚያም በኋላ እኔ አገልጋይህ ወደ ቤቴ ተመልሼ እንድሄድና በወላጆቼ መቃብር አጠገብ እንዳርፍ ፍቀድልኝ፤ እነሆ፥ ይህ ልጄ ኪምሀም ያገለግልሃል፤ ንጉሥ ሆይ! እርሱን ይዘኸው ሂድ፤ የወደድከውንም ለእርሱ አድርግለት።”
2 ሳሙኤል 19:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “እርሱን ይዤ እሄዳለሁ፤ እንዳደርግለት የምትፈልገውንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ለአንተም ቢሆን የምትጠይቀውን ሁሉ እፈጽማለሁ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “ከመዓም ከእኔ ጋራ ይሻገራል፤ አንተን ደስ የሚያሰኝህንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ከእኔ የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር ለአንተም አደርግልሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገዛ ከተማዬ ሞቼ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ እንድቀበር፥ እባክህ፥ አገልጋይህን አሰናብተውና ይመለስ፤ ነገር ግን አገልጋይህ ኪምሃም እነሆ፤ ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር ይሻገር፤ ደስ ያለህንም ነገር አድርግለት።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “ከመዓም ከእኔ ጋር ይሻገር፤ በፊቴ ደስ የሚያሰኘኝንም አደርግለታለሁ፤ አንተም ከእኔ የምትሻውን ነገር ሁሉ አደርግልሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ ከመዓም ከእኔ ጋር ይለፍ፥ ደስ የሚያሰኝህንም አደርግለታለሁ፥ አንተም ከእኔ የምትሻውን ሁሉ አደርግልሃለሁ አለው። |
ከዚያም በኋላ እኔ አገልጋይህ ወደ ቤቴ ተመልሼ እንድሄድና በወላጆቼ መቃብር አጠገብ እንዳርፍ ፍቀድልኝ፤ እነሆ፥ ይህ ልጄ ኪምሀም ያገለግልሃል፤ ንጉሥ ሆይ! እርሱን ይዘኸው ሂድ፤ የወደድከውንም ለእርሱ አድርግለት።”
“ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ የቸርነት ሥራ ስላደረጉልኝ ለገለዓዳዊው ለባርዚላይ ልጆች ግን መልካም ነገር በማድረግ ተንከባከባቸው፤ በማዕድህም ከሚመገቡት መካከል ይሁኑ።
እነርሱም የባቢሎን ንጉሥ ገዢ አድርጎ የሾመውን ገዳልያንን እስማኤል ስለ ገደለው ባቢሎናውያን አደጋ ያደርሱብናል ብለው ፈርተው ነበር፤ ስለዚህም ከባቢሎናውያን ፊት ሸሽተው ወደ ግብጽ ለመኰብለል ተነሡ፤ በቤተልሔም አጠገብ ባለችው ጌሩት ኪምሀም ተብላ በምትጠራው ቦታ ዕረፍት አደረጉ።