እነሆ፥ እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሰው ነኝ፤ የሚያስደስቱና የማያስደስቱ ነገሮችን መለየት እችላለሁን? የምበላውንም ሆነ የምጠጣውን ጣዕም መለየት እችላለሁን? ጆሮዬም የወንድና የሴት ዘፋኞችን ድምፅ መስማት ይችላልን? ንጉሥ ሆይ! በጌታዬ ላይ ለምን ተጨማሪ ሸክም እሆንብሃለሁ?
2 ሳሙኤል 19:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ንጉሡ ይህን ያኽል ታላቅ ወሮታ የሚከፍለኝ ለምንድን ነው? ነገር ግን የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሬ ከአንተ ጋር ጥቂት መንገድ ብቻ እሄዳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋይህ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ከንጉሡ ጋራ ጥቂት መንገድ ይሄዳል፤ ነገር ግን ንጉሡ በዚህ ሁኔታ ወሮታ የሚመልስልኝ ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሽማግሌ ነኝ፤ ታዲያ የሚያስደስቱና የማያስደስቱ ነገሮችን መለየት እችላለሁን? ከእንግዲህ አገልጋይህ የሚበላውንና የሚጠጣውን ጣዕሙን መለየት ይችላል? የሚዘፍኑትን የወንዶችና የሴቶችን ድምፅ አሁንስ መስማት እችላለሁ? ታዲያ አገልጋይህ ለንጉሥ ጌታዬ ለምን ተጨማሪ ሸክም ይሆናል? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ባሪያህ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ከንጉሡ ጋር ጥቂት ልሄድ ነበር፤ ንጉሡ እንዲህ ያለ ወረታ ለምን ይመልስልኛል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ባሪያህ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ከንጉሡ ጋር ጥቂት ልሄድ ነበር፥ ንጉሡ እንዲህ ያለ ወረታ ለምን ይመልስልኛል? |
እነሆ፥ እኔ አሁን የሰማንያ ዓመት ሰው ነኝ፤ የሚያስደስቱና የማያስደስቱ ነገሮችን መለየት እችላለሁን? የምበላውንም ሆነ የምጠጣውን ጣዕም መለየት እችላለሁን? ጆሮዬም የወንድና የሴት ዘፋኞችን ድምፅ መስማት ይችላልን? ንጉሥ ሆይ! በጌታዬ ላይ ለምን ተጨማሪ ሸክም እሆንብሃለሁ?
ከዚያም በኋላ እኔ አገልጋይህ ወደ ቤቴ ተመልሼ እንድሄድና በወላጆቼ መቃብር አጠገብ እንዳርፍ ፍቀድልኝ፤ እነሆ፥ ይህ ልጄ ኪምሀም ያገለግልሃል፤ ንጉሥ ሆይ! እርሱን ይዘኸው ሂድ፤ የወደድከውንም ለእርሱ አድርግለት።”
ዕድሜአችን ሰባ ዓመት ነው፤ ቢበዛም ሰማኒያ ዓመት ነው፤ እነዚያም ዘመናት በችግርና በሐዘን የተሞሉ ናቸው፤ ዕድሜአችን በቶሎ ያልቃል፤ እኛም እናልፋለን።
ስጡ፤ ለእናንተም ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ እንዲሁ ይሰፈርላችኋል፤ እንዲያውም በጥሩ መስፈሪያ ታምቆና ተጠቅጥቆ እስኪትረፈረፍ ድረስ ተሰፍሮ ይሰጣችኋል።”