“ወንድሜ ዮናታን ሆይ! እኔ ስለ አንተ በጣም አዘንኩ፤ አንተ ለእኔ በጣም ተወዳጅ ነበርክ። ፍቅርህ ለእኔ አስደናቂ ነበር፤ ይኸውም ከሴት ፍቅር የበረታ ነበር።
2 ሳሙኤል 19:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መፊቦሼትም “ንጉሥ ሆይ! ሁሉንም ሀብት ጺባ ይውሰደው፤ ለእኔ አንተ በሰላም ወደ ቤትህ መመለስህ ብቻ ይበቃኛል” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሜምፊቦስቴም ንጉሡን፣ “ንጉሥ ጌታዬ እንኳን በደኅና ተመለሰ እንጂ፣ እርሱ ሁሉንም ይውሰደው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፥ “ነገርህን ለምን ታበዛለህ? አንተና ጺባ እርሻውን ሁሉ እንድትካፈሉ አዝዣለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሜምፌቡስቴም ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሡ በደኅና ወደ ቤቱ ከተመለሰ እርሱ ሁሉን ይውሰደው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሜምፊቦስቴም ንጉሡን፦ ጌታዬ ንጉሡ በደኅና ወደ ቤቱ ከተመለሰ እርሱ ሁሉን ይውሰደው አለው። |
“ወንድሜ ዮናታን ሆይ! እኔ ስለ አንተ በጣም አዘንኩ፤ አንተ ለእኔ በጣም ተወዳጅ ነበርክ። ፍቅርህ ለእኔ አስደናቂ ነበር፤ ይኸውም ከሴት ፍቅር የበረታ ነበር።
እነርሱም ንጉሡንና ተከታዮቹን በጀልባ አጅበው ወደ ማዶ ለማድረስና ንጉሡ የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገሩ። ንጉሡ ወንዙን ለመሻገር ሲዘጋጅ ሳለ የጌራ ልጅ ሺምዒ መጥቶ በፊቱ ተዘረጋና እንዲህ አለ፤
ከዚህ በኋላ ንጉሡ የሳኦልን አገልጋይ ጺባን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “የሳኦልና የቤተሰቡ ንብረት የነበረውን ማናቸውንም ነገር የጌታህ የልጅ ልጅ ለሆነው ለመፊቦሼት እሰጣለሁ፤
የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል ለማስተማር ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን የማገልገል ግዴታ ከፈጸምኩ ለሕይወቴ ዋጋ አልሰጠውም፤ ለነፍሴም አልሳሳለትም።
በፍጹም እንደማላፍር በተስፋ እጠባበቃለሁ፤ ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና ዛሬ በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ።