ዳዊት፥ አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በዐመፅ መተባበሩን በሰማ ጊዜ “እግዚአብሔር ሆይ! የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት እንድትለውጥበት እለምንሃለሁ!” ሲል ጸለየ።
2 ሳሙኤል 17:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሑሻይም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በአሁኑ ሰዓት አኪጦፌል የሰጣችሁ ምክር ጥሩ አይደለም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኩሲም አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “አኪጦፌል የሰጠው ምክር በዚህ ጊዜ የሚያዋጣ አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሑሻይም አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “አኪጦፌል የሰጠው ምክር በዚህ ጊዜ መልካም አይደለም፤” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኩሲም አቤሴሎምን አለው፥ “አኪጦፌል በዚህ ጊዜ የመከራት ምክር መልካም አይደለችም። ይችውም አንዲት ናት።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኩሲም አቤሴሎምን፦ አኪጦፌል በዚህ ጊዜ የመከራት ምክር መልካም አይደለችም አለው። |
ዳዊት፥ አኪጦፌል ከአቤሴሎም ጋር በዐመፅ መተባበሩን በሰማ ጊዜ “እግዚአብሔር ሆይ! የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት እንድትለውጥበት እለምንሃለሁ!” ሲል ጸለየ።
አንተ እኔን ልትረዳኝ የምትችለው ግን ወደ ከተማይቱ ተመልሰህ አቤሴሎምን፥ አባትህን እንዳገለገልኩ አንተንም በታማኝነት አገለግላለሁ ብለህ ብትነግረው እንዲሁም አኪጦፌል የሚሰጠውን ምክር ሁሉ ብትቃወምልኝ ነው፤
አኪጦፌልም አቤሴሎምን እንዲህ አለው፦ “ቤት እንዲጠብቁ ከተዋቸው ከአባትህ ቁባቶች ጋር ተገናኝ በዚህም እስራኤላውያን ሁሉ አባትህን እንዳዋረድከው ያውቃሉ፤ ከአንተም ጋር ያሉት ሰዎች ሁሉ ስሜታቸው ይበረታታል።”
ሑሻይም በደረሰ ጊዜ አቤሴሎም “አኪጦፌል የሰጠን ምክር ይህ ነው፤ ይህንኑ ምክር እንከተል ወይስ ምን ማድረግ እንደሚገባን አንተም የምትነግረን አለ ይሆን?” ሲል ጠየቀው።