La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 17:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አቤሴሎምና እስራኤላውያን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ በተሻገሩ ጊዜ ዳዊት ማሕናይም ተብላ ወደምትጠራው ትንሽ ከተማ ደርሶ ነበር፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አቤሴሎም ከመላው የእስራኤል ሰዎች ጋራ ዮርዳኖስን ሲሻገር፣ ዳዊት ግን መሃናይም ደርሶ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤሴሎም ከመላው የእስራኤል ሰዎች ጋር ዮርዳኖስን ሲሻገር፥ ዳዊት ግን ማሕናይም ደርሶ ነበር።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም ወደ ምና​ሄም መጣ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም፥ ከእ​ርሱ ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም ወደ መሃናይም መጣ፥ አቤሴሎምም ከእርሱም ጋር የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 17:24
5 Referencias Cruzadas  

እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ።


ባያቸውም ጊዜ “እግዚአብሔር ከሠራዊቱ ጋር የሚሠፍርበት ቦታ ነው” አለ፤ ስለዚህ ያንን ቦታ ማሕናይም ብሎ ጠራው።


የሳኦል ሠራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር ከሳኦል ልጅ ከኢያቡስቴ ጋር የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ማሕናይም ሸሽቶ ሄደ፤


አንቺ ሱላማዊት ሆይ! ነዪ ተመለሺ፤ በደንብ አድርገን እንድንመለከትሽ ነዪ ተመለሺ። ሱላማጢስን በሁለት ሠራዊት መካከል እንደሚደረግ ጭፈራ የምትመለከቱአት ለምንድን ነው?


የምድራቸውም ስፋት ከሐሴቦን ተነሥቶ እስከ ራማት ምጽጳና እስከ ቤጦኒም እንዲሁም ከማሕናይም ተነሥቶ እስከ ሎዴባር ድንበር ይደርሳል፤