አንተ እኔን ልትረዳኝ የምትችለው ግን ወደ ከተማይቱ ተመልሰህ አቤሴሎምን፥ አባትህን እንዳገለገልኩ አንተንም በታማኝነት አገለግላለሁ ብለህ ብትነግረው እንዲሁም አኪጦፌል የሚሰጠውን ምክር ሁሉ ብትቃወምልኝ ነው፤
2 ሳሙኤል 17:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአቤሴሎም ባለሟሎች ወደዚያ ቤት መጥተው ሴቲቱን “አሒማዓጽና ዮናታን የት ናቸው?” ሲሉ ጠየቁአት። እርስዋም “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ስትል መለሰች። ሰዎቹም ፈልገው ሊያገኙአቸው ስላልቻሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአቤሴሎም ሰዎች እዚያ ቤት ወደ ሴቲቱ ዘንድ መጥተው፣ “አኪማአስና ዮናታን የት አሉ?” ብለው ጠየቁ። ሴቲቱም፣ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ብላ መለሰችላቸው፤ እነርሱም ፈልገው ስላጧቸው፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአቤሴሎም ሰዎች እዚያ ቤት ወደ ሴቲቱ ዘንድ መጥተው፥ “አሒማዓጽና ዮናታን የት አሉ?” ብለው ጠየቋት። ሴቲቱም፥ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ብላ መለሰችላቸው፤ እነርሱም ፈልገው ስላጧቸው፥ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአቤሴሎምም አገልጋዮች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥተው፥ “አኪማሆስና ዮናታን የት አሉ?” አሉ፤ ሴቲቱም፥ “ፈፋውን ተሻግረው ሄዱ፤ ጥቂትም ቀደሙአችሁ” አለቻቸው። እነርሱም ፈልገው አጡአቸው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአቤሴሎም ባሪያዎች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥተው፦ አኪማአስና ዮናታን የት አሉ? አሉ፥ ሴቲቱም፦ ፈፋውን ተሻግረው ሄዱ አለቻቸው። እነርሱም ፈልገው ባላገኙአቸው ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። |
አንተ እኔን ልትረዳኝ የምትችለው ግን ወደ ከተማይቱ ተመልሰህ አቤሴሎምን፥ አባትህን እንዳገለገልኩ አንተንም በታማኝነት አገለግላለሁ ብለህ ብትነግረው እንዲሁም አኪጦፌል የሚሰጠውን ምክር ሁሉ ብትቃወምልኝ ነው፤
እነርሱም “የዕብራውያን ሴቶች እንደ ግብጻውያን ሴቶች አይደሉም፤ እነርሱ ብርቱዎች ስለ ሆኑ አዋላጆች ወደ እነርሱ ገና ከመምጣታቸው በፊት ያለምንም ችግር ይወልዳሉ” ሲሉ መለሱለት።
ዳዊትም ለካህኑ ለአቢሜሌክ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ እዚህ የመጣሁት የንጉሥ ሳኦልን ተልእኮ ለመፈጸም ነው፤ እኔ ወደዚህ የተላክሁበትን ጉዳይ ለማንም ሰው እንዳልገልጥ ንጉሡ አዞኛል፤ ተከታዮቼንም በአንድ ቦታ እንድንገናኝ አዝዣቸዋለሁ፤