አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ከንጉሥ ዳዊት አማካሪዎች አንዱ የሆነውን አኪጦፌል ተብሎ የሚጠራውን ሰው መልእክተኛ በመላክ ከጊሎ ከተማ አስጠራ፤ በንጉሡ ላይ የተጠነሰሰው ሤራ እየጠነከረ፥ የአቤሴሎምም ተከታዮች ቊጥር እየጨመረ ሄደ።
2 ሳሙኤል 16:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ወደ አኪጦፌል መለስ ብሎ “እነሆ እኛ አሁን በዚህ ተገኝተናል፤ ታዲያ ምን እንድናደርግ ትመክረናለህ?” ሲል ጠየቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎምም አኪጦፌልን፤ “እስኪ ምክር አምጣ፤ ምን እናድርግ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤሴሎምም አኪጦፌልን፤ “እስቲ ምክር አምጣ፤ ምን እናድርግ?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም አኪጦፌልን፦ ምን እንደምናደርግ ምከሩ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም አኪጦፌልን፦ ምከሩ፥ ምን እናድርግ? አለው። |
አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ከንጉሥ ዳዊት አማካሪዎች አንዱ የሆነውን አኪጦፌል ተብሎ የሚጠራውን ሰው መልእክተኛ በመላክ ከጊሎ ከተማ አስጠራ፤ በንጉሡ ላይ የተጠነሰሰው ሤራ እየጠነከረ፥ የአቤሴሎምም ተከታዮች ቊጥር እየጨመረ ሄደ።
አኪጦፌልም አቤሴሎምን እንዲህ አለው፦ “ቤት እንዲጠብቁ ከተዋቸው ከአባትህ ቁባቶች ጋር ተገናኝ በዚህም እስራኤላውያን ሁሉ አባትህን እንዳዋረድከው ያውቃሉ፤ ከአንተም ጋር ያሉት ሰዎች ሁሉ ስሜታቸው ይበረታታል።”
ከዚህም የተነሣ ከጠላቶቻችን ጋር ተባብረው ከወጉን በኋላ ከአገሪቱ አምልጠው መሄድ ይችላሉ፤ ስለዚህ ቊጥራቸው እየበዛ እንዳይሄድ ኑ፤ አንድ ዘዴ እንፈልግ።”
ዕቅዳቸውን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ ወደ ጥልቅ ቦታ ለሚሄዱ በጨለማ የሠሩትንም ሥራ “ማን ያይብናል? ማን ያውቅብናል?” ለሚሉ ሰዎች ወዮላቸው!
የጦር ዕቅድንም አውጡ፤ ነገር ግን እናንተ እንዳሰባችሁት አይሳካላችሁም፤ የፈለጋችሁትን ያኽል ተናገሩ፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምክራችሁ አይጸናም።