ከዚህ በኋላ ዳዊትና ሠራዊቱ ባመሩበት መንገድ ተጓዙ፤ ሺምዒም በኮረብታው ጥግ እነርሱን ተከትሎ እየሄደ በመራገም ድንጋይና ዐፈር በእነርሱ ላይ ይወረውር ነበር።
2 ሳሙኤል 16:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናልባት እግዚአብሔር መከራዬን አይቶ በእርሱ ርግማን ፈንታ በረከትን ይሰጠኝ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናልባትም እግዚአብሔር ሐዘኔን አይቶ በዛሬውም ርግማን ፈንታ በጎ ነገር ያደርግልኝ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ምናልባት በዚህ ቀን መከራዬን አይቶ ስለ እርግማኑ መልካም ይመልስልኛል” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምናልባት መከራዬን አይቶ ስለ ርግማኑ በዚህ ቀን መልካም ይመልስልኛል” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምናልባት በዚህ ቀን መከራዬን አይቶ ስለ እርግማኑ መልካም ይመልስልኛል አላቸው። |
ከዚህ በኋላ ዳዊትና ሠራዊቱ ባመሩበት መንገድ ተጓዙ፤ ሺምዒም በኮረብታው ጥግ እነርሱን ተከትሎ እየሄደ በመራገም ድንጋይና ዐፈር በእነርሱ ላይ ይወረውር ነበር።
የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባለሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢውን ይቀጣ ይሆናል፤ ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ለተረፉት ሰዎች እባክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።”
አምላክ ሆይ! አንተ ግን ችግርንና ጭንቀትን አይተህ ልታስወግዳቸው መፍትሔ ታዘጋጃለህ፤ ችግረኛ ራሱን ለአንተ ይሰጣል፤ አንተም የሙት ልጆችን ትረዳለህ።
ምናልባት እግዚአብሔር አምላካችሁ ቊጣውን መልሶ፥ በረከቱን ይሰጣችሁ ይሆናል፤ እናንተም በዚያን ጊዜ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቊርባን ታቀርባላችሁ።
ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክህ እርሱን ማዳመጥ አልፈለገም፤ ይልቁንም እግዚአብሔር አንተን ስለሚወድህ መርገሙን ወደ በረከት ለወጠው። እግዚአብሔር እናንተን ይወዳችኋል።
አሁን መከራን ለምትቀበሉትም ከእኛ ጋር ዕረፍትን ይሰጣችኋል። ይህም የሚሆነው ጌታ ኢየሱስ ከኀያላን መላእክቱ ጋር ከሰማይ በሚወርድበት ጊዜ ነው፤
ሐናም እንዲህ ስትል ስእለት ተሳለች፦ “የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! እኔን አገልጋይህን ተመልከተኝ! መከራዬንም በማየት አስበኝ! አትርሳኝም! አንድ ወንድ ልጅ ብትሰጠኝ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ለአንተ የተለየ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ጠጒሩም ከቶ አይላጭም።”