በርከት ካሉ ዓመቶች በኋላ የሴዋ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች፤ ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከወዳጁ ከዐዱላማዊው ከሒራ ጋር በጎቹን ወደሚሸልቱ ሰዎች ወደ ቲምና ሄደ።
2 ሳሙኤል 13:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ንጉሥ ዳዊትም ሄዶ “ንጉሥ ሆይ! በጎቼን እየሸለትሁ ነው፤ ስለዚህ አንተና መኳንንትህ መጥታችሁ የግብዣው ተካፋዮች እንድትሆኑልኝ ትፈቅዳለህን?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “እነሆ፤ ባሪያህ በጎቹን እየሸለተ ነው፤ ታዲያ ንጉሡና ሹማምቱ ፈቃዳቸው ሆኖ እባክህ ይገኙልኝ?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ንጉሡም ሄዶ፥ “እነሆ፤ አገልጋይህ በጎቹን ይሸልታል፤ ንጉሡና ሹማምንቱ ፈቃዳቸው ሆኖ እባክህ ይገኙልኝ?” ሲል ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ መጥቶ፥ “እነሆ፥ አገልጋይህ በጎቹን ያሸልታል፤ ንጉሡ ከአገልጋይህ ጋር ይሂድ፤ አገልጋዮቹም ይሂዱ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ መጥቶ፦ እነሆ፥ ባሪያህ በጎቹን ያሸልታል፥ ንጉሡና ሎሌዎቹ ከባሪያህ ጋር ይሂዱ አለው። |
በርከት ካሉ ዓመቶች በኋላ የሴዋ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች፤ ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከወዳጁ ከዐዱላማዊው ከሒራ ጋር በጎቹን ወደሚሸልቱ ሰዎች ወደ ቲምና ሄደ።
ከሁለት ዓመት በኋላ አቤሴሎም በኤፍሬም ከተማ አጠገብ በዓለ ሐጾር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በጎቹን ይሸልት ነበር፤ ስለዚህም የንጉሡን ወንዶች ልጆች ሁሉ ለግብዣ ወደዚያ ጠራ።
ንጉሡም “ልጄ ሆይ! መምጣት አያስፈልገንም፤ እኛ ሁላችን ከመጣን መስተንግዶው ይከብድብሃል” ሲል መለሰለት፤ አቤሴሎምም አጥብቆ ጠየቀ፤ ንጉሡ ግን አሳቡን መለወጥ ስላልፈቀደ አቤሴሎምን መርቆ አሰናበተው።
ንግግሩ እንደ ቅቤ የለዘበ ነው፤ በልቡ የሚያስበው ግን ጦርነትን ነበር አንደበቱ ከዘይት ይበልጥ የለሰለሰ ነው፤ ነገር ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ነው።
በጎችህንም እንደምታሸልት ሰምቶአል፤ እረኞችህ ከእኛ ጋር በነበሩበት ጊዜም ሁሉ ምንም ዐይነት ጒዳት እንዳላደረስንባቸው እንድታውቅ ይፈልጋል፤ በቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ ከመንጋቸው አንድ እንኳ አልተወሰደባቸውም፤