La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 10:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዐሞናውያን ተሰልፈው ወጥተው የእነርሱ ዋና ከተማቸው በሆነችው በራባ መግቢያ በር አጠገብ ስፍራቸውን ያዙ፤ ሌሎቹ ሶርያውያን፥ ከጦብና ከማዕካ የመጡት ጦረኞች በአንድ ሜዳማ ቦታ ስፍራቸውን ያዙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሞናውያን ወጥተው በከተማቸው መግቢያ በር ላይ ተሰለፉ፤ የሱባና የረአብ ሶርያውያን እንዲሁም የጦብና የመዓካ ሰዎች ለብቻ ሜዳው ላይ ተሰለፉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሞናውያን ወጥተው በከተማቸው መግቢያ በር ላይ ተሰለፉ፤ የጾባና የረሖብ ሶርያውያን እንዲሁም የጦብና የመዓካ ሰዎች ለብቻ ሜዳው ላይ ተሰለፉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ሞ​ንም ልጆች ወጥ​ተው በበሩ መግ​ቢያ ፊት ለፊት ይዋጉ ጀመሩ፤ የሱ​ባና የሮ​ዖብ ሶር​ያ​ው​ያን፥ የአ​ስ​ጦ​ብና የአ​ማ​ሌ​ቅም ሰዎች ለብ​ቻ​ቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአሞንም ልጆች ወጥተው በበሩ መግቢያ ፊት ለፊት ተሰለፉ፥ የሱባና የረአብ ሶርያውያን፥ የጦብና የመዓካም ሰዎች ለብቻቸው በሰፊ ሜዳ ላይ ነበሩ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 10:8
13 Referencias Cruzadas  

ዐሞናውያን ዳዊትን በገዛ እጃቸው ጠላት እንዳደረጉት ተገነዘቡ፤ ስለዚህም እግረኛ ወታደሮችን ከቤትረሖብና ከጾባ ኻያ ሺህ ሶርያውያንንና ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን፤ እንዲሁም ከንጉሥ ማዕካ አንድ ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ፤


ዳዊትም ስለዚህ ጉዳይ ሰምቶ ከመላው ሠራዊት ጋር ኢዮአብን በእነርሱ ላይ አዘመተ፤


ኢዮአብ የጠላት ሠራዊት ከፊትና ከኋላ በኩል አደጋ እንደሚጥልበት ተመለከተ፤ ስለዚህ ከእስራኤል ወታደሮች ጀግኖች የሆኑትን መርጦ በሶርያውያን ፊት ለፊት አመች በሆነ ስፍራ መደባቸው፤


የሸፍቶች አለቃ ሆኖ ነበር፤ ይህም የሆነው ዳዊት ሀዳድዔዜርን ድል ነሥቶ የእርሱ ጦር ተባባሪዎች የሆኑትን ሶርያውያንን ከፈጀ በኋላ ነበር፤ ረዞንና ተከታዮቹም ወደ ደማስቆ ሄዱ፤ በዚያም ሲኖሩ እርሱን የሶርያ ንጉሥ እንዲሆን አደረጉት፤


የተከራዩአቸው ሠላሳ ሁለት ሺህ ሠረገሎችና የንጉሥ ማዕካ ሠራዊት መጥተው በሜዳባ አጠገብ ሰፈሩ፤ ዐሞናውያንም ከየከተሞቻቸው ወጥተው ለጦርነት ተዘጋጁ።


ዐሞናውያንም ተሰልፈው መጥተው የእነርሱ ዋና ከተማ በሆነችው በራባ መግቢያ በር አጠገብ ስፍራቸውን ያዙ፤ እነርሱን ሊረዱ የመጡ ነገሥታትም ገላጣማ በሆነው ገጠር ስፍራቸውን ያዙ።


ስለዚህ የነታንያ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬሐ ልጆች ዮሐናንና ዮናታን፥ የታንሑሜት ልጅ ሠራያ፥ ከነጦፋ የዔፋይ ልጆች፥ ከማዕካም የዛንያ ከሰዎቻቸው ሁሉ ጋር በምጽጳ ወደሚገኘው ወደ ገዳልያ መጡ።


ስለዚህ ሰዎቹ ወደ ሰሜን ሄዱ፤ በአገሪቱም ከሚገኘው ከጺን ምድረ በዳ ጀምረው ለሐማት መተላለፊያ ቅርብ እስከሆነው ረሖብ ድረስ አጠኑ።


ወደ ዔብሮን፥ ረሖብ፥ ሐሞንና ቃና አልፎ እስከ ታላቁ ሲዶና ይደርሳል።


የአሴር ነገድ በዓኮ፥ በሲዶና፥ በአሕላብ፥ በአክዚብ፥ በሔልባ፥ በአፌቅና በረሖብ ይኖሩ የነበሩትን ኗሪዎች አላባረሩም ነበር።


ዮፍታሔም ከወንድሞቹ ሸሽቶ ጦብ ተብላ በምትጠራ ምድር ኖረ፤ እዚያ ጥቂት ወሮበሎች ተሰብስበው ተከተሉት።


ይህም በሆነ ጊዜ የገለዓድ መሪዎች ዮፍታሔን ከጦብ ምድር መልሰው ለማምጣት ሄዱ።