ዳዊትም ዐማሌቃዊውን “ይህን ጥፋት በራስህ ላይ ያመጣህ አንተው ራስህ ነህ፤ እግዚአብሔር መርጦ የቀባውን ንጉሥ ገድያለሁ ብለህ በተናገርክ ጊዜ በራስህ ላይ ፈርደሃል” አለው።
2 ሳሙኤል 1:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሚወድቅበት ጊዜ እንደሚሞት ዐውቅ ስለ ነበር ወደ እርሱ ቀርቤ ገደልኩት፤ ከዚህ በኋላ ዘውዱን ከራሱ ላይ፥ አንባሩንም ከክንዱ ላይ ወሰድኩ፤ ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ እነርሱን ለአንተ አመጣሁልህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መቼም ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፣ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና የክንዱን አንባር ወስጄ እነሆ፤ ለጌታዬ አምጥቻለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፥ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና በክንዱ ላይ የነበረውን አንባር ወስጄ፥ እነሆ ለጌታዬ አምጥቻለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ከወደቀ በኋላ አለመዳኑን አይቼ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱም ላይ የነበረውን ዘውድ፥ በክንዱም የነበረውን ቢተዋ ወሰድሁ፤ ወደዚህም ወደ ጌታዬ አመጣሁት።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ከወደቀ በኋላ አለ መዳኑን አይቼ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፥ በራሱም ላይ የነበረውን ዘውድ በክንዱም የነበረውን ቢተዋ ወሰድሁ፥ ወደዚህም ወደ ጌታዬ አመጣሁት። |
ዳዊትም ዐማሌቃዊውን “ይህን ጥፋት በራስህ ላይ ያመጣህ አንተው ራስህ ነህ፤ እግዚአብሔር መርጦ የቀባውን ንጉሥ ገድያለሁ ብለህ በተናገርክ ጊዜ በራስህ ላይ ፈርደሃል” አለው።
ዳዊት የዐሞናውያን አምላክ ከሆነው ሚልኮም ተብሎ ከሚጠራው ጣዖት ራስ ላይ ሠላሳ አምስት ኪሎ ግራም የሚመዝነውንና በውስጡም የከበረ ዕንቊ ያለበትን ዘውድ ወስዶ በራሱ ላይ ደፋው፤ እንዲሁም ከከተማይቱ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤
ከዚያም በኋላ ዮዳሄ ኢዮአስን አውጥቶ በራሱ ላይ ዘውድ ጫነበት፤ ለመንግሥቱ መመሪያ የሆነውንም ሕግ አንድ ቅጂ አስረከበው፤ በዚህ ዐይነት ኢዮአስ ተቀብቶ ነገሠ፤ ሕዝቡም እያጨበጨበ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ!” አለ።
አዶኒቤዜቅም “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር ፍርፋሪ እየለቀሙ ይበሉ ነበር፤ በእነርሱ ላይ የፈጸምኩትን ግፍ ዛሬ እግዚአብሔር በእኔ ላይ መልሶ አመጣብኝ” ሲል ተናገረ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተወስዶ በዚያው ሞተ።
እርሱም የጦር መሣሪያ አንጋቹን ወጣት በፍጥነት በመጥራት፥ “ሰይፍህን መዘህ ግደለኝ፤ ሴት ገደለችው እንድባል አልፈልግም” ሲል አዘዘው። ስለዚህ ወጣቱ በሰይፍ መትቶ ገደለው።
ስለዚህም ሳኦል ዶይቅን “አንተው ግደላቸው!” አለው፤ ኤዶማዊው ዶይቅም ተነሥቶ ሁሉንም ገደለ፤ በዚያኑ ቀን የፈጃቸው ኤፉድ የሚለብሱ ካህናት ብዛት ሰማኒያ አምስት ነበር፤