Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 11:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚያም በኋላ ዮዳሄ ኢዮአስን አውጥቶ በራሱ ላይ ዘውድ ጫነበት፤ ለመንግሥቱ መመሪያ የሆነውንም ሕግ አንድ ቅጂ አስረከበው፤ በዚህ ዐይነት ኢዮአስ ተቀብቶ ነገሠ፤ ሕዝቡም እያጨበጨበ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ!” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ዮዳሄም የንጉሡን ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነለት፤ ኪዳኑንም ሰጠው፤ መንገሡን ዐወጁ፤ ቀብተውም አነገሡት። ከዚያም ሕዝቡ፣ “ንጉሡ ሺሕ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በማጨብጨብ ደስታቸውን ከፍ ባለ ድምፅ ገለጹ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ከዚያም በኋላ ዮዳሄ ኢዮአስን አውጥቶ በራሱ ላይ ዘውድ ጫነበት፤ ለመንግሥቱ መመሪያ የሆነውንም ሕግ አንድ ቅጂ አስረከበው፤ በዚህ ዓይነት ኢዮአስ ተቀብቶ ነገሠ፤ ሕዝቡም እያጨበጨበ ድምፁን ከፍ አድርጎ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ!” አለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አው​ጥቶ ዘው​ዱን ጫነ​በት፤ ምስ​ክ​ሩ​ንም ሰጠው፤ ቀብ​ቶም አነ​ገ​ሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ” እያሉ በእ​ጃ​ቸው አጨ​በ​ጨቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብተውም ንጉሥ አደረጉትና “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ!” እያሉ እጃቸውን አጨበጨቡ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 11:12
45 Referencias Cruzadas  

ሳሙኤልም ሕዝቡን “እግዚአብሔር የመረጠው ሰው እነሆ ይህ ነው! ከእኛም መካከል እርሱን የሚስተካከለው የለም” አለ። ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ ይሁን!” አሉ።


ከዚህም በኋላ እኔ የምሰጥህን፥ ትእዛዞቹ የተጻፉባቸውን ሁለት ጽላቶች በታቦቱ ውስጥ አኑር።


ካህኑ ሳዶቅም ከተቀደሰው ድንኳን ይዞት የመጣውን የቅባት ዘይት መያዣ ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው፤ በዚህን ጊዜ እምቢልታ ነፉ፤ ሕዝቡም ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ ሰሎሞን!” አሉ፤


በሚወድቅበት ጊዜ እንደሚሞት ዐውቅ ስለ ነበር ወደ እርሱ ቀርቤ ገደልኩት፤ ከዚህ በኋላ ዘውዱን ከራሱ ላይ፥ አንባሩንም ከክንዱ ላይ ወሰድኩ፤ ጌታዬ ሆይ! እነሆ፥ እነርሱን ለአንተ አመጣሁልህ።”


እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።


“እናንተም ከባቢሎን በደስታ ወጥታችሁ፥ በሰላም ወደ ሀገራችሁ እንድትመለሱ ትደረጋላችሁ፤ ተራራዎችና ኰረብቶች በፊታችሁ በመዘመር ይፈነድቃሉ፤ የሜዳ ዛፎችም በእጆቻቸው ያጨበጭባሉ።


እናንተ ወንዞች አጨብጭቡ፤ እናንተ ተራራዎች በእግዚአብሔር ፊት እልል እያላችሁ በአንድነት ዘምሩ።


ሕዝቦች ሁሉ፥ በደስታ አጨብጭቡ! ከፍ ባለ ድምፅ በመዘመር፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ!


ከእርስዋም እጅ ማምለጥ የቻለ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ ብቻ ነበር፤ እርሱም እንኳ ከሌሎቹ ጋር እንዲገደል ተመክሮበት ነበር፤ ነገር ግን አክስቱ የነበረችው በአባትዋ በኩል የንጉሥ አካዝያስ እኅት የሆነችው፥ የንጉሥ ኢዮራም ልጅ ይሆሼባዕ በመደበቅ ከሞት አዳነችው፤ እርስዋም እርሱንና ሞግዚቱን ወስዳ በቤተ መቅደሱ ግቢ በሚገኘው ማረፊያ ክፍል ውስጥ ስለ ደበቀችው በዐታልያ እጅ ሳይገደል ቀረ።


የዳዊት ታማኝ ወዳጅ ሑሻይ አቤሴሎምን ባገኘው ጊዜ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ይሁን!” እያለ ጮኸ።


ሳሙኤል የወይራ ዘይት መያዣውን ቀንድ ወስዶ በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም። ከዚያም በኋላ “እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ መሪ እንድትሆን ቀባህ፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ነግሠህ በዙሪያቸው ካሉ ጠላቶች ታድናቸዋለህ እግዚአብሔር በርስቱ ላይ የሾመህ ለመሆኑ ይህ ማስረጃ ነው፤


ዐይኖቹ የእሳት ነበልባል ይመስላሉ፤ በራሱም ላይ ብዙ ዘውዶች አሉ፤ ከእርሱ በቀር ሌላ ማንም የማያውቀው በእርሱ ላይ የተጻፈ ስም ነበረ፤


አሁን ግን ከመላእክት ጥቂት ጊዜ ዝቅ ብሎ የነበረውን፥ የሞትን መከራ በመቀበሉ ምክንያት የክብርና የምስጋና ዘውድ የጫነውን ኢየሱስን እናያለን፤ እርሱ በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሁላችን ሞቶአል።


ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃንም ጠላህ፤ በዚህ ምክንያት እግዚአብሔር አምላክህ መረጠህ፤ ከጓደኞችህም ይበልጥ ደስታን በሚሰጥ ቅባት ቀባህ” ይላል።


እኛን ከእናንተ ጋር በክርስቶስ እንድንጸና ያደረገን እግዚአብሔር ነው፤ ለሥራ የለየንም እርሱ ነው፤


“በእርግጥም ሄሮድስና ጴንጤናዊ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው መሲሕ ባደረግኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሡ፤


የእሾኽ አክሊልም ጐንጒነው በራሱ ላይ ደፉበት፤ በቀኝ እጁም የመቃ ዘንግ አስያዙት፤ በፊቱም እየተንበረከኩ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ ያፌዙበት ነበር፤


ከሕዝቡም ፊት ለፊት ይሄዱ የነበሩትና ከኋላ ይከተሉ የነበሩት፥ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ምስጋና ይሁን! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሳዕና! ምስጋና በአርያም ለእግዚአብሔር ይሁን!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


ዳንኤልም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ንጉሥ ሆይ! ለዘለዓለም ኑር!


ንጉሡን ናቡከደነፆርንም እንዲህ አሉት፦ “ንጉሥ ሆይ! ለዘለዓለም ኑር!


በሕዝቦች መካከል በእርሱ ጥላ ሥር እንኖራለን ብለን ያሰብነውን እግዚአብሔር የቀባውን የሕይወት እስትንፋሳችን አጠመዱብን።


ይህን ቃል ባይናገሩ በእርግጥ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም።


ምስክርነቱን ጠብቀህ ያዝ፤ በደቀ መዛሙርቴ ልብ ውስጥም ሕጉን አትም።


ጠላቶቹ ኀፍረትን እንዲከናነቡ አደርጋቸዋለሁ፤ እርሱ ግን የሚያንጸባርቅ ዘውድ ይቀዳጃል።


ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን አፍርሰሃል፤ ዘውዱንም በዐፈር ላይ ጥለኸዋል።


እርሱ ሥርዓትን ለያዕቆብ ልጆች ዐወጀ፤ ለእስራኤልም ሕግን መሠረተ፤ ልጆቻቸውንም እንዲያስተምሩ የቀድሞ አባቶቻችንን አዘዛቸው።


በብዙ በረከትን ሰጥተህ ተቀበልከው፤ በራሱ ላይ የንጹሕ ወርቅ ዘውድ ደፋህለት።


ንጉሡም ከሌሎቹ ልጃገረዶች ሁሉ አስበልጦ ወደዳት፤ ከሌሎቹም ሁሉ ይበልጥ በፊቱ ሞገስንና መወደድን አገኘች፤ እርሱም መንግሥታዊውን ዘውድ አንሥቶ በራስዋ ላይ ደፋላትና በአስጢን ቦታ አነገሣት።


ከዚህ በኋላ ዮዳሄ ኢዮአስን አውጥቶ በራሱ ላይ ዘውድ ጫነበት፤ ለመንግሥቱ መመሪያ የሆነውንም ሕግ አንድ ቅጅ አስረከበው፤ በዚህ ዐይነት ካህኑ ዮዳሄና ልጆቹ ኢዮአስን ቀብተው አነገሡት፤ ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ!” በማለት ደስታቸውን ገለጡ።


ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ለንጉሡ ክብር ዘቦችና ለቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ሁሉ ኀላፊዎች ወደሆኑት የጦር መኰንኖች ሁሉ ልኮ ወደ ቤተ መቅደስ እንዲመጡ አስጠራቸው፤ በዚያም ሊያደርገው ያቀደውን ይስማሙበት ዘንድ በመሐላ እንዲያረጋግጡለት አደረገ፤ ከዚያም በኋላ የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን አሳያቸውና፥


ይህን የወይራ ዘይት በራሱ ላይ አፍስስበት፤ ‘አንተ ተቀብተህ በእስራኤል ላይ እንድትነግሥ እግዚአብሔር አዞአል’ ብለህም ንገረው፤ ከዚህም በኋላ በሩን በመክፈት በተቻለ ፍጥነት ከዚያ ስፍራ ተነሥተህ ሽሽ።”


በዚያም ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን ቀብተው በእስራኤል ላይ ያንግሡት፤ ከዚህ በኋላ እምቢልታ በመንፋት ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ‘ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ ሰሎሞን!’ በሉ።


ዳዊት የዐሞናውያን አምላክ ከሆነው ሚልኮም ተብሎ ከሚጠራው ጣዖት ራስ ላይ ሠላሳ አምስት ኪሎ ግራም የሚመዝነውንና በውስጡም የከበረ ዕንቊ ያለበትን ዘውድ ወስዶ በራሱ ላይ ደፋው፤ እንዲሁም ከከተማይቱ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤


እንግዲህ የእስራኤል መሪዎች ሁሉ በኬብሮን ወደ ነበረው ወደ ዳዊት የመጡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ እርሱም ከእነርሱ ጋር በእግዚአብሔር ፊት የቃል ኪዳን ስምምነት አደረገ፤ እነርሱም ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።


እንግዲህ ጠንክሩ! በርቱም! ጌታችሁ ሳኦል ሞቶአል፤ የይሁዳ ሕዝብ እኔን ቀብቶ አንግሦኛል።”


ከዚህ በኋላ የይሁዳ ሰዎች ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትንም ቀብተው የይሁዳ ንጉሥ አደረጉት። ዳዊት ገለዓዳውያን የሆኑ የያቤሽ ሰዎች ሳኦልን እንደ ቀበሩት በሰማ ጊዜ፥


ሳሙኤልም በወይራ ዘይት የተሞላውን ቀንድ ወስዶ ዳዊትን በወንድሞቹ ፊት ቀባው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት አደረበት፤ ከዚያም ቀን ጀምሮ ከእርሱ አልተለየም፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤል ወደ ራማ ተመለሰ።


በአባቴ በንጉሥ ዳዊት ላይ የፈጸምከውን በደል ሁሉ በደንብ ታውቃለህ፤ አንተ ስላደረግኸው ክፉ ነገር እግዚአብሔር ራሱ ይቀጣሃል፤


ጭፍሮቹም ሰይፋቸውን እንደ መዘዙ ንጉሡን ከአደጋ ለመከላከል በመሠዊያው በኩል በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ዙሪያውን እንዲሰለፉ አደረጋቸው።


አዶንያስ በዛሬው ዕለት ብዙ ጥጆችንና የሰቡ ኰርማዎችን፥ በጎችን ዐርዶ መሥዋዕት አቅርቦአል፤ ሌሎቹን የንጉሡን ልጆች የሠራዊትህን አዛዥ ኢዮአብንና ካህኑን አብያታርን ጋብዞአል፤ እነሆ አሁን በዚህ ሰዓት “ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ አዶንያስ!” በማለት እየደነፉ ከእርሱ ጋር በመብላትና በመጠጣት ላይ ናቸው።


ወዲያውኑ የኢዩ ጓደኞች የነበሩት የጦር መኰንኖች ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፤ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ኢዩ ነግሦአል!” ሲሉ ጮኹ።


ሕይወትን እንድትሰጠው ለመነህ፤ አንተም ረጅም ዕድሜና ዘለዓለማዊ የሆነ ሕይወትን ሰጠኸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios