እነርሱም የመጣላቸውን ኰርማ ወስደው ለመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ። “ባዓል ሆይ! እባክህ ስማን!” እያሉም ጮኹ። በሠሩትም መሠዊያ እየዘለሉ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም።
2 ነገሥት 4:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግያዝም ወደ ፊት ቀድሞአቸው ሄደና የኤልሳዕን ምርኲዝ በልጁ ፊት ላይ አኖረ፤ ነገር ግን ድምፅም ሆነ ሌላ የሕይወት ምልክት አልነበረም፤ ስለዚህም ተመልሶ ሄዶ ኤልሳዕን “ልጁ አልተነሣም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግያዝም ቀድሟቸው ሄዶ በትሩን በልጁ ፊት ላይ አደረገ፤ ነገር ግን ድምፅም፣ ምላሽም አልነበረም። ስለዚህ ግያዝ ወደ ኤልሳዕ ተመልሶ፣ “ልጁ አልነቃም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግያዝም ወደ ፊት ቀድሞአቸው ሄደና የኤልሳዕን ምርኲዝ በልጁ ፊት ላይ አኖረ፤ ነገር ግን ድምፅም ሆነ ሌላ የሕይወት ምልክት አልነበረም፤ ስለዚህም ተመልሶ ሄዶ ኤልሳዕን “ልጁ አልተነሣም” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግያዝም በፊታቸው ይሄድ ነበር፤ ግያዝም ቀድሞአቸው ደረሰ፤ በትሩንም በሕፃኑ ፊት ላይ አኖረው፤ ነገር ግን ድምፅ ወይም መስማት አልነበረም፤ እርሱንም ሊገናኘው ተመልሶ፥ “ሕፃኑ አልተነሣም” ብሎ ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግያዝም ቀደማቸው፤ በትሩንም በሕፃኑ ፊት ላይ አኖረው፤ ነገር ግን ድምፅ ወይም መስማት አልነበረም፤ እርሱንም ሊገናኘው ተመልሶ “ሕፃኑ አልነቃም፤” ብሎ ነገረው። |
እነርሱም የመጣላቸውን ኰርማ ወስደው ለመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ። “ባዓል ሆይ! እባክህ ስማን!” እያሉም ጮኹ። በሠሩትም መሠዊያ እየዘለሉ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም።
እኩለ ቀን ካለፈም በኋላ የሠርክ መሥዋዕት እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ እየተራወጡ ይቀባጥሩ ነበር፤ ይሁን እንጂ ምንም መልስ አላገኙም፤ ድምፅም አልተሰማም።
የኤልሳዕ አገልጋይ የሆነው ግያዝ፥ “ጌታዬ ንዕማንን ምንም ነገር ሳያስከፍል አሰናብቶታል፤ ያ ሶርያዊ ሰው ያቀረበለትን ስጦታ መቀበል ይገባው ነበር፤ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፥ በፍጥነት በመሮጥ ተከትየው ሄጄ ከእርሱ አንድ ነገር ማግኘት አለብኝ” ሲል በልቡ አሰበ።
ልጅዋን ከሞት ያስነሣላትን፥ በሱነም ትኖር የነበረችውን ሴት እነሆ፥ ኤልሳዕ አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፥ “እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቈይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ።”
“የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ልባቸውን ለጣዖቶች ሰጥተዋል፤ በደላቸው በፊታቸው እንቅፋት እንዲሆንባቸው አድርገዋል፤ ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ የእኔን ፈቃድ መጠየቃቸው ተገቢ ነውን?”
ሞተው ዐፈር የበላቸው ሁሉ ይነሣሉ፤ ከእነርሱም ከፊሎቹ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሲገቡ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ዘለዓለማዊ ኀፍረትና ውርደት ይላካሉ።
ሳኦልም “በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ እንጣልባቸውን? ድልንስ ለእኛ ትሰጣለህን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያን ቀን ምንም መልስ አልሰጠም።
ስለዚህም ምን ማድረግ እንደሚገባው እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔር ግን በሕልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አማካይነት መልስ እንዲሰጠው አልፈቀደም።