2 ነገሥት 24:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአቄም ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢኮንያን ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአቄምም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ ልጁ ዮአኪንም በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአቄም ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢኮንያን ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአቄምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በኦዛም የአትክልት ቦታ ተቀበረ ልጁም ዮአኪን በእርሱ ፋንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአቄምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ልጁም ዮአኪን፤ በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
ንጉሥ ኢዮአቄም ያደረገው ሁሉ፥ አጸያፊ የሆነው ልማዱና የፈጸመው ክፉ ነገር ጭምር፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጻሕፍት ተመዝግቦ ይገኛል፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢኮንያን ነገሠ።
ለኢዮአቄም ልጅ ለኢኮንያን እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦ “እኔ ሕያው አምላክ አንተ በቀኝ እጄ እንደሚገኝ የማኅተም ቀለበት ብትሆን እንኳ አውልቄ እጥልሃለሁ፤
ንጉሥ ኢዮአቄም ሆይ! እነሆ እግዚአብሔር ስለ አንተ የሚለው ይህ ነው፦ ‘ከዘርህ በዳዊት መንግሥት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ከቶ አይኖርም፤ ሬሳህም የትም ተጥሎ ለቀን ፀሐይ ሐሩርና ለሌሊት ቊር የተጋለጠ ይሆናል፤