2 ነገሥት 23:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እዚያ በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ። የይሁዳም ሰዎችም የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን መረጡ፤ ቀብተውም አነገሡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢዮስያስም አገልጋዮች ከመጊዶ ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው በገዛ መቃብሩ ቀበሩት። የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን ወስደው ቀቡት፤ በአባቱም ምትክ አነገሡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እዚያ በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ። የይሁዳም ሰዎችም የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን መረጡ፤ ቀብተውም አነገሡት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮቹም በድኑን በሰረገላው አድርገው ከመጊዶ ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤ በመቃብሩም ቀበሩት። የሀገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ዮአክስን ወሰዱት። ቀብተውም በአባቱ ፋንታ አነገሡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሞተም በኋላ ባሪያዎቹ በሠረገላው አድርገው ከመጊዶ ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤ በመቃብሩም ቀበሩት። የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን ወሰዱት፤ ቀብተውም በአባቱ ፋንታ አነገሡት። |
ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም ላይ የማመጣው ቅጣት አንተ በዐይንህ ሳታየው እስከምትሞትበት ጊዜ ድረስ ተፈጻሚ አይሆንም፤ ስለዚህም አንተ በሰላም እንድትሞት አደርጋለሁ።’ ” ሰዎቹም ይህን መልእክት ይዘው ወደ ንጉሥ ኢዮስያስ ተመለሱ።
ንጉሥ ኢዮስያስ ለቤተ መቅደሱ ይህን ሁሉ ካደራጀ በኋላ፥ የግብጽ ንጉሥ ኒካዑ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ በሚገኘው ካርከሚሽ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ላይ አደጋ ለመጣል ሠራዊቱን አሰልፎ መጣ፤ ኢዮስያስም ሊቋቋመው ተነሣ፤
እነርሱም ከሠረገላው አውጥተው እዚያ በነበረው በሌላ ሠረገላ ውስጥ በማስቀመጥ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት፤ በዚያም ሞተ፤ በነገሥታትም መካነ መቃብር ተቀበረ፤ የይሁዳና የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች ሁሉ አለቀሱለት።
የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ስለ ንጉሥ ኢዮስያስ አታልቅሱ፤ በመሞቱም አትዘኑ፤ ነገር ግን የኢዮስያስ ልጅ ሻሉም፤ ዳግመኛ ወደማይመለስበት ቦታ ስለሚወሰድ፥ የትውልድ አገሩንም ዳግመኛ ስለማያይ፥ ለእርሱ ምርር ብላችሁ አልቅሱ።
በአባቱ ምትክ በይሁዳ ስለ ነገሠው ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሻሉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዳግመኛ ወደማይመለስበት ወደ ሩቅ አገር ይሄዳል፤