La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 18:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ታዲያ ይህ ከሆነ የሐማትና የአርፋድ አማልክት የት አሉ? የሰፋርዋይም የሄናዕና የዒዋ አማልክትስ የት ደረሱ? ከእነርሱ አንዱ እንኳ ሰማርያን ከእጄ ማዳን ችሎአልን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይም፣ የሄናና የዒዋም አማልክት ታዲያ የት ደረሱ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ታዲያ ይህ ከሆነ የሐማትና የአርፋድ አማልክት የት አሉ? የሰፋርዋይም የሄናዕና የዒዋ አማልክትስ የት ደረሱ? ከእነርሱ አንዱ እንኳ ሰማርያን ከእጄ ማዳን ችሎአልን?

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የኤ​ማ​ትና የአ​ር​ፋድ አማ​ል​ክት ወዴት አሉ? የሴ​ፋ​ሩ​ዋ​ይ​ምና የሄና የዒ​ዋም አማ​ል​ክት ወዴት አሉ? ስማ​ር​ያን ከእጄ አድ​ነ​ዋ​ታ​ልን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይምና የሄና የዒዋም አማልክት ወዴት አሉ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን?

Ver Capítulo



2 ነገሥት 18:34
12 Referencias Cruzadas  

የሐማት ንጉሥ ቶዒ ዳዊት የሀዳድዔዜርን ሠራዊት በሙሉ ድል ማድረጉን ሰማ።


ይኸውም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ሰልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ በእስረኛነት ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹ በሐላሕ ከተማ፥ ጥቂቶቹ በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በሐቦር ወንዝ አጠገብ፥ እንዲሁም ሌሎቹ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ።


የካልኖን፥ የካርከሚሽን፥ የሐማትንና የአርፋድን ከተሞች ድል አድርጌአለሁ፤ ሰማርያንና ደማስቆንም በቊጥጥሬ ሥር አድርጌአለሁ።


የሐማት፥ የአርፋድ፥ የሰፋርዋይም የሄናዕና የዒዋ ከተሞች ነገሥታት አሁን ወዴት አሉ?”


“የሐማትና የአርፋድ ከተማ ነዋሪዎች የደማስቆን የጥፋት ወሬ ስለ ሰሙ ግራ ተጋቡ፤ ወደ ላይና ወደ ታች እንደሚናወጥ ባሕር የእነርሱም ልብ ተሸበረ።


እስቲ ወደ ካልኔ ከተማ ሄዳችሁ ተመልከቱ፤ ከዚያም አልፋችሁ “ሐማት” ተብላ ወደምትጠራው ታላቂቱ ከተማና የፍልስጥኤማውያን ከተማ ወደሆነችው ወደ ጋት ውረዱ፤ እናንተ ከእነርሱ ትበልጣላችሁን? ግዛታችሁስ ከእነርሱ ግዛት ይበልጣልን?


ስለዚህ ሰዎቹ ወደ ሰሜን ሄዱ፤ በአገሪቱም ከሚገኘው ከጺን ምድረ በዳ ጀምረው ለሐማት መተላለፊያ ቅርብ እስከሆነው ረሖብ ድረስ አጠኑ።