2 ነገሥት 15:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዖዝያ ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በቀድሞ አባቶቹ መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአታም ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓዛርያስ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ በአባቶቹ መቃብር አጠገብ ቀበሩት። ልጁ ኢዮአታምም በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዖዝያ ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በቀድሞ አባቶቹ መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአታም ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓዛርያስም እንደ አባቶቹ አንቀላፋ፥ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓዛርያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፤ ልጁም ኢዮአታም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
ዖዝያ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዳግማዊ ኢዮርብዓም ልጅ ዘካርያስ በእስራኤል ነገሠ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ስድስት ወር ገዛ፤
ዖዝያ ሞተ፤ በነገሥታትም መካነ መቃብር አጠገብ ባለው ስፍራ ቀበሩት፤ በነገሥታት መካነ መቃብር ያልተቀበረው የቆዳ በሽታ ስለ ነበረበት ነው፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአታም ነገሠ።
ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን አየሁት፤ እርሱም ከፍ ባለና ልዕልና ባለው ዙፋን ላይ ተቀምጦ መጐናጸፊያውም ቤተ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።
ዖዝያን፥ ኢዮአታም፥ አካዝና ሕዝቅያስ በይሁዳ ተከታትለው በነገሡባቸው ዘመናት፤ እንዲሁም የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረበት ዘመን፥ እግዚአብሔር ለብኤር ልጅ ለሆሴዕ የገለጠለት የትንቢት ቃል ይህ ነው።