2 ነገሥት 11:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮዳሄም በቤተ መቅደስ ተቀምጠው ይጠበቁ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች አውጥቶ ለጦር አለቆቹ ሰጣቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች ለመቶ አለቆቹ ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮዳሄም በቤተ መቅደስ ተቀምጠው ይጠበቁ የነበሩትን የንጉሥ ዳዊትን ጦሮችና ጋሻዎች አውጥቶ ለጦር አለቆቹ ሰጣቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮዳሄም በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ሰይፍና ጦር ሁሉ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የንጉሡን የዳዊትን ጋሻና ጦር ሁሉ ለመቶ አለቆች ሰጣቸው። |
ንጉሥ ሰሎሞን የቤተ መቅደሱን ሥራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ አባቱ ዳዊት ለእግዚአብሔር የተለዩ ያደረጋቸውን ብርና ወርቅ እንዲሁም ሌሎችን ዕቃዎች ሁሉ በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚገኘው የዕቃ ግምጃ ቤት አኖራቸው።
አቤሜሌክም “በኤላ ሸለቆ የገደልከው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ በእኔ ዘንድ አለ፤ እርሱም ከኤፉዱ በስተኋላ በጨርቅ ተጠቅሎ ተቀምጦአል፤ የምትፈልገው ከሆነ ውሰደው፤ በዚህ የሚገኝ የጦር መሣሪያ እርሱ ብቻ ነው” አለው። ዳዊትም “እርሱኑ ስጠኝ! ከእርሱ የተሻለ ሰይፍ የትም አይገኝም” አለው።