ዘመንህ ተፈጽሞ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በምታርፍበት ጊዜ ከአብራክህ የሚወጣውን ልጅህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ የእርሱንም መንግሥት አጸናለሁ።
2 ነገሥት 10:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢዩ ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአካዝ ነገሠ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዩ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በሰማርያ ቀበሩት። ልጁ ኢዮአካዝም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኢዩ ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ኢዮአካዝ ነገሠ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዩም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ቀበሩት። በፋንታውም ልጁ ኢዩአካዝ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዩም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ቀበሩት። በፋንታውም ልጁ ኢዮአካዝ ነገሠ። |
ዘመንህ ተፈጽሞ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በምታርፍበት ጊዜ ከአብራክህ የሚወጣውን ልጅህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፤ የእርሱንም መንግሥት አጸናለሁ።
ሮብዓም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በነገሥታቱ መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም እግር ልጁ አቢያ ተተክቶ ነገሠ። የሮብዓም እናት ናዕማ ተብላ የምትጠራ ዐሞናዊት ነበረች።
ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ኢዩን “በአክዓብ ተወላጆች ሁሉ ላይ ልታደርግ የሚገባህን ባዘዝኩህ መሠረት ፈጽመሃል፤ ከዚህም የተነሣ የአንተ ትውልድ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ላይ እንደሚነግሡ የተስፋ ቃል እሰጥሃለሁ” አለው።
የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሦስተኛው ዓመት የኢዩ ልጅ ኢዮአካዝ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ መኖሪያውንም በሰማርያ አድርጎ ዐሥራ ሰባት ዓመት ገዛ፤