ንጉሡም ለሦስተኛ ጊዜ ከኀምሳ ሰዎች ጋር ሌላ መኰንን ላከ፤ ይህኛው መኰንን ግን ወደ ኰረብታው በመውጣት በኤልያስ ፊት በጒልበቱ ተንበርክኮ እንዲህ ሲል ለመነ፤ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት ሰዎች ምሕረት አድርግልን! ሕይወታችንንም ከሞት አድን!
2 ነገሥት 1:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎቹን ሁለት መኰንኖችና ተከታዮቻቸውን ሁሉ ከሰማይ የወረደ እሳት በልቶአቸዋል፤ ለእኔ ግን እባክህ ምሕረት አድርግልኝ!” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ እሳት ከሰማይ ወርዳ፣ የፊተኞቹን ሁለት ዐምሳ አለቆችና ሰዎቻቸውን ሁሉ በላች፤ አሁን ግን ሕይወቴ በፊትህ የከበረች ትሁን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌሎቹን ሁለት መኰንኖችና ተከታዮቻቸውን ሁሉ ከሰማይ የወረደ እሳት በልቶአቸዋል፤ ለእኔ ግን እባክህ ምሕረት አድርግልኝ!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ እሳት ከሰማይ ወርዳ የፊተኞቹን ሁለቱን የአምሳ አለቆችና አምሳ አምሳውን ሰዎቻቸውን በላች፤ አሁን ግን ነፍሴ በፊትህ የከበረች ትሁን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ እሳት ከሰማይ ወርዳ የፊተኞቹን ሁለቱን የአምሳ አለቆችና አምሳ አምሳፍ ሰዎቻቸውን በላች፤ አሁን ግን ነፍሴ በፊትህ የከበረች ትሁን፤” ብሎ ለመነው። |
ንጉሡም ለሦስተኛ ጊዜ ከኀምሳ ሰዎች ጋር ሌላ መኰንን ላከ፤ ይህኛው መኰንን ግን ወደ ኰረብታው በመውጣት በኤልያስ ፊት በጒልበቱ ተንበርክኮ እንዲህ ሲል ለመነ፤ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት ሰዎች ምሕረት አድርግልን! ሕይወታችንንም ከሞት አድን!
በዚህም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ኤልያስን “ከእርሱ ጋር አብረህ ውረድ፤ ከቶም አትፍራ” አለው። ስለዚህም ኤልያስ ከመኰንኑ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ፤
የእግዚአብሔርን የጸጋ ወንጌል ለማስተማር ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልኩትን የማገልገል ግዴታ ከፈጸምኩ ለሕይወቴ ዋጋ አልሰጠውም፤ ለነፍሴም አልሳሳለትም።
ሳኦልም “በእርግጥ ተሳስቻለሁ፤ ልጄ ዳዊት ሆይ! ተመልሰህ ወደ እኔ ና፤ ዳግመኛ ልጐዳህ ከቶ አልፈልግም፤ በዛሬይቱ ሌሊት ሕይወቴን አትርፈሃል፤ እኔ እንደ ሞኝ ሆኜአለሁ! ከባድ የሆነ ስሕተትም ፈጽሜአለሁ!” ሲል መለሰ።