15 የቅዱሳን ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው።
15 የቅዱሳኑ ሞት፣ በእግዚአብሔር ፊት የተከበረ ነው።
15 የቅዱሳኑ ሞት በጌታ ፊት የከበረ ነው።
የስንዴ እሸት እስኪጐመራ በማሳ ላይ እንደሚቈይ አንተም በዕድሜ እስከምትሸመግል ትኖራለህ።
የእነርሱ ሕይወት በእርሱ ዘንድ ውድ ስለ ሆነ ከጭቈናና ከዐመፅ ያድናቸዋል።
“ከዚህም በኋላ ድኻው ሰው ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም አጠገብ ወሰዱት፤ እንዲሁም ሀብታሙ ሰው ሞተና ተቀበረ።
እኔም ሕያው ነኝ፤ ሞቼ ነበር፤ ነገር ግን እነሆ፥ ለዘለዓለም ሕያው ነኝ፤ በሞትና በሲኦል ላይ ሥልጣን አለኝ።
በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች፥ በሽማግሌዎችም ፊት መቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ ይህን መዝሙር ከምድር ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራቱ ሺህ ሰዎች በቀር ማንም ሊማረው አልቻለም።
ማንም ሰው በአንተ ላይ አደጋ ጥሎ ሊገድልህ ቢፈልግ አንድ ሰው ውድ የሆነ ሀብቱን እንደሚጠብቅ አምላክህ እግዚአብሔር አንተን በሰላም ይጠብቅሃል፤ ስለ ጠላቶችህም የሆነ እንደ ሆነ አንድ ሰው ድንጋዩን ከወንጭፍ እንደሚያስፈነጥር እግዚአብሔር ራሱ አሽቀንጥሮ ይጥላቸዋል።