ሚክያስም “አንተ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነዋ!” አለው፤ ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ “በዚህ የምትገኙ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ!” አለ።
2 ነገሥት 1:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ!” አለው፤ በዚያም ጊዜ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወርዶ መኰንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልያስም መልሶ የዐምሳ አለቃውን፣ “እኔ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንሁ፣ እሳት ከሰማይ ወርዳ፣ አንተንና ዐምሳውን ሰዎችህን ትብላ!” አለው። ከዚያም እሳት ከሰማይ ወርዳ የዐምሳ አለቃውንና ሰዎቹን ፈጽማ በላች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልያስም “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ!” አለው፤ በዚያም ጊዜ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወርዶ መኰንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልያስም መልሶ የአምሳ አለቃውን፥ “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፤ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ” አለው። እሳትም ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳውን ሰዎች በላች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልያስም መልሶ የአምሳ አለቃውን “እኔስ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ሆንሁ እሳት ከሰማይ ትውረድ፤ አንተንም፥ አምሳውንም ሰዎችህን ትብላ፤” አለው። እሳትም ከሰማይ ወርዳ እርሱንና አምሳ ሰዎቹን በላች። |
ሚክያስም “አንተ በደኅና ከተመለስክማ እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት አልተናገረም ማለት ነዋ!” አለው፤ ቀጥሎም ድምፁን ከፍ በማድረግ “በዚህ የምትገኙ ሕዝቦች ሁሉ እኔ የተናገርኩትን ሁሉ ልብ ብላችሁ አድምጡ!” አለ።
ንጉሡም እንደገና ሌላውን መኰንን ከኀምሳ ሰዎች ጋር ላከ፤ እርሱም ወደ ኤልያስ ወጥቶ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አሁኑኑ ወርደህ ወደ እርሱ እንድትመጣ ንጉሡ አዞሃል!” አለው።
እስራኤላውያን ግን በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሳለቁ፤ በነቢያቱም በማፌዝ፥ የእግዚአብሔርን ቃል አቃለሉ፤ ከዚህም የተነሣ፥ የእግዚአብሔር ቊጣ በሕዝቡ ላይ ወረደ፤ ከታላቅ ቊጣውም ለማምለጥ አልቻሉም።
የመጀመሪያው መልእክተኛ ንግግሩን ገና ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጣና “በጎቹንና እረኞቹን በሙሉ መብረቅ ከሰማይ ወርዶ ገደላቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።
ንጉሡ በሰጠው ጥብቅ ትእዛዝ መሠረት እሳቱ በኀይል ተቀጣጥሎ ይነድ ስለ ነበር ሲድራቅን፥ ሚሳቅንና አብደናጎን ወደ እሳቱ የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን አቃጥሎ ገደላቸው።
ንጉሡም “እነሆ፥ እኔ እሳቱ ምንም ሳይጐዳቸው ከእስራት ተፈተው በነበልባሉ ውስጥ የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል” አለ።
ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።
እስራኤላውያን ስለ ደረሰባቸው ችግር ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ እግዚአብሔርም የማጒረምረም ጩኸታቸውን ሰምቶ እጅግ በመቈጣት የሚባላ እሳት ላከባቸው፤ ያም እሳት ከሰፈሩ አንዱን ክፍል አወደመ።
እነርሱም “የእነዚህን ክፉ ሰዎች ፍጻሜ የከፋ ያደርገዋል። የወይኑንም ተክል ቦታ ፍሬውን በየጊዜው ለሚሰጡት ለሌሎች ገበሬዎች ያከራያል” አሉት።
ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ባዩ ጊዜ፥ “ጌታ ሆይ! ከሰማይ እሳት ወርዶ እነዚህን ሰዎች ያቃጥላቸው ዘንድ እንድናዝዝ ትፈቅዳለህን?” አሉት።
ሄሮድስም በበኩሉ ጴጥሮስን አስፈልጎ ባጣው ጊዜ ዘብ ጠባቂዎችን ከመረመረ በኋላ እንዲገደሉ አዘዘ፤ ከዚህም በኋላ ሄሮድስ ከይሁዳ ወደ ቂሳርያ ሄዶ እዚያ ተቀመጠ።