2 ቆሮንቶስ 7:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የተዋረዱትን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ሐዘንተኞችን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ኀዘንተኞችን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ያዘኑትን የሚያጽናና እርሱ እግዚአብሔር በቲቶ መምጣት አጽናናን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ኀዘንተኞችን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን፤ |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የማጽናናችሁ እኔ ራሴ ነኝ፤ ታዲያ እንደ ሣር የሚጠወልገውንና መሞት ያለበትን ሰውን የምትፈሩት ለምንድን ነው?
ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።
“እኔ ሥራቸውን ሁሉ ተመልክቼአለሁ፤ ይሁን እንጂ እፈውሳቸዋለሁ፤ እመራቸዋለሁ፤ እኔ ለእነርሱና ስለ እነርሱ ለሚያለቅሱት ሙሉ መጽናናትን እሰጣለሁ።
ልጃገረዶቻቸውም በደስታ ይጨፍራሉ፤ ወንዶች ወጣቶችና ሽማግሌዎችም ደስ ይላቸዋል፤ አጽናናቸዋለሁ፤ ለቅሶአቸውን ወደ ደስታ፥ ሐዘናቸውንም ወደ ሐሴት እለውጣለሁ፤
ከመጽናናታችንም በላይ ቲቶ ባገኘው ደስታ ይበልጥ ተደስተናል፤ የተደሰትነውም ሁላችሁም ቲቶን ስላጽናናችሁትና መንፈሱንም ስላሳረፋችሁት ነው።
በእናንተ የነበረኝን ትምክሕት ለቲቶ ነግሬው ነበር፤ እናንተም አላሳፈራችሁኝም፤ ሁልጊዜ እውነትን እንነግራችሁ ነበር፤ ይህም ስለ እናንተ ለቲቶ የነገርነው ትምክሕት እውነት በመሆኑ ተረጋግጦአል።
የተጽናናነውም በእርሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን እናንተ እርሱን ያጽናናችሁት መሆኑን በመስማታችንም ጭምር ነው፤ ስለ እኔ ያላችሁን ናፍቆትና ሐዘን ጭንቀትም በነገረን ጊዜ ይበልጥ ደስ አለኝ።
በክርስቶስ መበረታታት ካላችሁ፥ በፍቅሩም የተጽናናችሁ ከሆነ፥ ከመንፈስ ቅዱስም ጋር ኅብረት ካላችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ደግነትንና ርኅራኄን ካሳያችሁ፥
ወንድማችንንና የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን፥ የክርስቶስን መልካም ዜና በማብሠር የሥራ ጓደኛችንን ጢሞቴዎስን ልከንላችኋል፤ የላክንላችሁም እንዲያጸናችሁና በእምነት እንድትበረቱ እንዲመክራችሁ ነው፤