እኔ እርሱን በተንሠራፉ ቅርንጫፎች የተዋበ አደረግሁት፤ እርሱ እኔ እግዚአብሔር በተከልኳት በዔደን ገነት ያለውን ዛፍ ሁሉ የሚያስቀና ነበር።’
2 ቆሮንቶስ 12:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ወደ ገነት ተነጥቆ በሰው ቃል ሊገለጥና ሰውም ሊናገረው የማይችለውን ነገር ሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ወደ ገነት እንደ ተነጠቀ፣ በዚያም በሰው አንደበት ሊገለጥ የማይችል፣ ሰውም እንዲናገረው ያልተፈቀደለት ነገር ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ገነት ተነጠቀ፤ በሰው አንደበት ሊገለጥ የማይችለውን፥ ሰውም ሊናገር ያልተፈቀደለትን ነገር ሰማ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ገነትም ነጥቀው ወሰዱት፤ በዚያም ሰው ሊናገረው የማይችለውን የማይተረጐም ነገር ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ገነት ተነጠቀ፥ ሰውም ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ። |
እኔ እርሱን በተንሠራፉ ቅርንጫፎች የተዋበ አደረግሁት፤ እርሱ እኔ እግዚአብሔር በተከልኳት በዔደን ገነት ያለውን ዛፍ ሁሉ የሚያስቀና ነበር።’
እርሱም የሰው እጅ የሚመስል ነገር ወደ እኔ ዘርግቶ የራስ ጠጒሬን ያዘ፤ በዚሁ ራእይ የእግዚአብሔር መንፈስ ከምድር ወደ ሰማይ አነሣኝና ወደ ኢየሩሳሌም አደረሰኝ። በሰሜን በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ በሚያስገባው ቅጽር በር አሳልፎ የእግዚአብሔርን ቅናት የሚቀሰቅስን የጣዖት ምስል ወዳለበት ስፍራ አደረሰኝ።
የክርስቶስ የሆነ አንድ ሰው ዐውቃለሁ፤ ይህ ሰው ከዐሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ተወሰደ፤ (የተወሰደውም ከነሥጋው ይሁን ወይም አይሁን አላውቅም፤ እግዚአብሔር ያውቃል።)
ከዚህ በኋላ እኛ በሕይወት የምንገኘው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ ለዘለዓለምም ከጌታ ጋር እንሆናለን።
“መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ‘ድል ለሚነሣ በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካለው ከሕይወት ዛፍ ፍሬ እንዲበላ አደርገዋለሁ።’