2 ቆሮንቶስ 10:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ራሳችንን ልናወዳድር ወይም ራሳችንን ልናነጻጽር አንደፍርም፤ እነርሱ ግን ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር በማመዛዘናቸውና ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር በማወዳደራቸው አስተዋዮች አይደሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ሰዎች ጋራ ራሳችንን ልንመድብ ወይም ልናነጻጽር አንደፍርም፤ እነርሱ ራሳቸውን በራሳቸው ሲመዝኑና ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋራ ሲያነጻጽሩ አስተዋዮች አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን መቁጠር ወይም ራሳችንን ማስተያየት አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ እርስ በራሳቸው ሲያመዛዝኑ፥ እርስ በራሳቸውም ሲተያዩ፥ አስተዋይ አይደሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ራሳቸውን በአሰቡትና በገመገሙት መጠን ራሳቸውን ከሚያመሰግኑት ሰዎች ጋር ራሳችንን ልንቈጥር፥ ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርም፤ እነርሱ ራሳቸውም የሚናገሩትን ትርጕሙን አያውቁትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም። |
“ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ ሲል በልቡ ጸለየ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኔ እንደ ሌሎች ሰዎች ቀማኛ፥ ግፈኛ አመንዝራ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ፤ ይልቁንም እንደዚህ እንደ ቀራጭ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ።
ይህን የሚሉ ሰዎች እኛ በሩቅ ሆነን በመልእክቶቻችን በምንጽፈውና በቅርብም ከእናንተ ጋር ሆነን በምንሠራው መካከል ምንም ልዩነት አለመኖሩን ይገንዘቡ።
እንደገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ለእናንተ ወይም ከእናንተ የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን?
በልብ ባለው ሳይሆን በሚታየው ለሚመኩ መልስ ለመስጠት እንድትችሉ በእኛ ትመኩ ዘንድ ዕድል እንሰጣችኋለን እንጂ እንደገና እኛ ለእናንተ ራሳችንን አናመሰግንም።