2 ቆሮንቶስ 1:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲያውም ሞት እንደ ተፈረደብን ያኽል ተሰምቶን ነበር፤ ይህም ሁሉ የደረሰብን፥ የምንተማመነው ሙታንን በሚያስነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን ኀይል አለመሆኑን እንድንገነዘብ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥም የሞት ፍርድ እንደ ተፈረደብን ይሰማን ነበር፤ ይህም የሆነው ሙታንን በሚያስነሣ በእግዚአብሔር እንድንታመን እንጂ፣ በራሳችን እንዳንታመን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርግጥም፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ የሞት ፍርድ እንደተላለፈብን በውስጣችን ተሰምቶን ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙታንን በሚያስነሣቸው በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን በውስጣችን ለመሞት ቈርጠን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አዎን፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር። |
ጻድቅ ሰው በእርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ብለውም እርሱ ግን ‘የቀድሞ የጽድቅ ሥራዬ ይበቃኛል’ ብሎ ኃጢአት መሥራት ቢጀምር፥ ከቀድሞ መልካም ሥራው አንዱንም እንኳ አላስታውስለትም፤ ስለዚህም በኃጢአቱ ምክንያት ይሞታል።
ወንድሞች ሆይ! በእስያ ክፍለ ሀገር በነበርንበት ጊዜ የደረሰብንን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ ይህም የደረሰብን መከራ ልንሸከመው ከምንችለው በላይ ወድቆብን ስለ ነበር በሕይወት ለመኖር የነበረን ተስፋ እንኳ ተቋርጦ ነበር።
ነገር ግን ይህ ከሁሉ የሚበልጠው ኀይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ አለመሆኑ እንዲታወቅ ይህን ክቡር ነገር እንደ ሸክላ ዕቃ ሆነን ይዘነዋል።