2 ዜና መዋዕል 32:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰናክሬም በኢየሩሳሌምም ላይ አደጋ ለመጣል ያቀደ መሆኑን ንጉሥ ሕዝቅያስ በተገነዘበ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቅያስም ሰናክሬም መምጣቱንና ኢየሩሳሌምንም ለመውጋት ማሰቡን ባወቀ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቅያስም ሰናክሬም እንደመጣ፥ ኢየሩሳሌምንም ሊወጋ ፊቱን አንዳቀና ባየ ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስም ሰናክሬም እንደ መጣ፥ ኢየሩሳሌምንም ሊወጋ ፊቱን እንዳቀና አየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቅያስም ሰናክሬም እንደ መጣ፥ ኢየሩሳሌምንም ሊወጋ ፊቱን አንዳቀና ባየ ጊዜ፥ |
ንጉሥ ሕዝቅያስ እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል ብዙ ነገሮችን ካከናወነ በኋላ፥ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሰናክሬም ይሁዳን ወረረ፤ እንደሚያሸንፍ ተማምኖ የተመሸጉትን ከተሞች ከበበ
እርሱ ከባለሟሎቹ ባለሥልጣኖች ጋር ከከተማይቱ ውጪ ያሉትን ምንጮችና የውሃ መተላለፊያ ቦይ ለመድፈን ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት፤ ይህንንም ያደረጉት አሦራውያን ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረቡ ምንም ውሃ እንዳያገኙ ለማድረግ ነው፤ ስለዚህ ባለሥልጣኖቹ ብዙ ሰዎችን ወደዚያ በመውሰድ ከምንጮቹ ውሃ እንዳይፈስስ ለማድረግ፥ እነዚያን ምንጮች ሁሉ ደፈኑአቸው።
ስለዚህም ከሕዝባችን መካከል ሰይፍ፥ ጦርና ቀስት የያዙ ሰዎችን በየጐሣቸው በማዘጋጀት፥ ሥራው ባልተጠናቀቀበት ቦታ ሁሉ በቅጽሩ ግንብ በስተጀርባ እንዲመሸጉ አደረግሁ።