አንድ ቀን ከቀትር በኋላ ዘግየት ብሎ ዳዊት ከቀን እንቅልፉ ነቅቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወጣ፤ እዚያም ወዲያና ወዲህ ሲመላለስ ገላዋን የምትታጠብ አንዲት ሴት አየ፤ ሴትዮዋም በጣም ውብ ነበረች፤
1 ሳሙኤል 9:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማምለኪያውም ስፍራ ወርደው ወደ ከተማይቱ በገቡ ጊዜ በሳሙኤል ቤት ሰገነት ላይ ለሳኦል አልጋ ተዘጋጀለት፤ እርሱም እዚያ ተኝቶ ዐደረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማምለኪያው ኰረብታ ወደ ከተማዪቱ ከወረዱ በኋላ ሳሙኤል በቤቱ ሰገነት ላይ ከሳኦል ጋራ ተነጋገረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከማምለኪያው ኰረብታ ወደ ከተማዪቱ ከወረዱ በኋላ ሳሙኤል በቤቱ ሰገነት ላይ ከሳኦል ጋር ተነጋገረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባማ ኮረብታም ወደ ከተማዪቱ ወረዱ፤ ሳሙኤልም ለሳኦል በሰገነቱ ላይ መኝታ አዘጋጀለት፤ እርሱም ተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኮረብታውም መስገጃ ወደ ከተማይቱ ወረዱ፥ ሳሙኤልም ለሳኦል በሰገነቱ ላይ መኝታ አዘጋጀለት፥ እርሱም ተኛ። |
አንድ ቀን ከቀትር በኋላ ዘግየት ብሎ ዳዊት ከቀን እንቅልፉ ነቅቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወጣ፤ እዚያም ወዲያና ወዲህ ሲመላለስ ገላዋን የምትታጠብ አንዲት ሴት አየ፤ ሴትዮዋም በጣም ውብ ነበረች፤
ስለዚህም ሕዝቡ የዛፍ ቅጠል እየቈረጡ አምጥተው በሚኖሩበት ግቢ፥ በየቤታቸው ጣራ ድምድማት ላይ፥ በቤተ መቅደሱ አደባባይና የውሃ በር ተብሎ በሚጠራው አደባባይ፥ እንዲሁም በኤፍሬም አደባባይ ዳስ ጣሉ፤
የኢየሩሳሌም ሕዝብና የይሁዳ ነገሥታት የሚኖሩባቸው ቤቶች፥ እንዲሁም በጣራዎቻቸው ላይ ለሰማይ ሠራዊት ዕጣን የሚታጠንባቸውና ለባዕዳን አማልክትም የወይን ጠጅ የሚፈስባቸው ቤቶች ሁሉ እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ።”
ነገር ግን ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ሽባውን ወደ ቤት ማግባት አቃታቸው፤ ስለዚህ ወደ ጣራ ላይ ይዘውት ወጡ፤ ጣራውንም ከፍተው በመካከሉ አውርደው ሽባውን ከነአልጋው በኢየሱስ ፊት አኖሩት።
በነጋም ጊዜ ማለዳ ሳሙኤል ከሰገነቱ ላይ ሳኦልን ጠርቶ “እንግዲህ ተነሥ፤ ላሰናብትህና መንገድህን ቀጥል” አለው፤ ሳኦልም ከመኝታው ተነሣ፤ እርሱና ሳሙኤልም አብረው ወደ መንገዱ ሄዱ፤