1 ሳሙኤል 7:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በራማ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እየተመለሰ እዚያም የዳኝነት ሥራ ይሠራ ነበር፤ በዚህም በራማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በአርማቴም ወዳለው ቤቱ ይመለስ ነበር፤ በዚያም ደግሞ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር። በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በራማም ወዳለው ቤት ይመለስ ነበር፤ በዚያም ደግሞ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር። በዚያም ለጌታ መሠዊያ ሠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፤ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፥ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ። |
ያዕቆብ እዚያ መሠዊያ ሠርቶ “ኤል ቤትኤል” ብሎ ሰየመው፤ ከወንድሙ ፊት ሸሽቶ በሄደበት ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ስፍራ ነበር።
ይህችም ነቢይት በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማና በቤትኤል መካከል በሚገኘው የዲቦራ የተምር ዛፍ ሥር ተቀምጣ ትፈርድ ስለ ነበር የእስራኤል ሕዝብ ፍርድ ለማግኘት ወደ እርስዋ ይሄዱ ነበር።
ጌዴዎንም በዚያ መሠዊያ ሠርቶ “እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነው” ብሎ ሰየመው፤ (ይህም መሠዊያ እስከ ዛሬ የአቢዔዜር ጐሣ ይዞታ በሆነችው በዖፍራ ቆሞ ይገኛል።)
በኮረብታማው በኤፍሬም አገር ራማ ተብላ በምትጠራ ትንሽ ከተማ የሚኖር ትውልዱ ከኤፍሬም ነገድ የሆነ፥ ሕልቃና ተብሎ የሚጠራ አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም የይሮሐም ልጅ የኤሊሁ የልጅ ልጅ ሲሆን፥ ኤሊሁ ደግሞ የቶሑ ልጅ የጹፍ የልጅ ልጅ ነበር፤
በማግስቱም ሕልቃናና ቤተሰቡ በማለዳ ተነሥተው ለእግዚአብሔር ከሰገዱ በኋላ በራማ ወደሚገኘው ቤታቸው ሄዱ፤ ሕልቃናም ከሚስቱ ከሐና ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እግዚአብሔርም አስታወሳት፤
ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልጌላ ሄደው በእግዚአብሔር ፊት የሳኦልን ንጉሥነት አጸደቁ፤ በእግዚአብሔርም ፊት የአንድነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ በዓሉንም ሳኦልና መላው ሕዝብ በታላቅ ደስታ አከበሩት።
እነሆ፥ ሳሙኤል ከሞተ ቈየት ብሎአል፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ለእርሱ በማዘን አልቅሰው በሚኖርባት በራማ ቀብረውታል፤ ቀደም ሲል ሳኦል ጠንቋዮችንና ሙታን ጠሪዎችን ከእስራኤል ምድር እንዲባረሩ አስገድዶአቸው ነበር።