እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል በርትተን እንዋጋ! እንግዲህ ሁሉ ነገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!”
1 ሳሙኤል 4:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን ሆይ! እንግዲህ በርቱ! ጠንክሩ! ይህ ካልሆነ ቀድሞ እነርሱ የእኛ ባሪያዎች እንደ ነበሩ ሁሉ እኛም ደግሞ የዕብራውያን ባርያዎች ሆነን መቅረታችን ነው፤ ስለዚህ በወንድነት ጠንክራችሁ ተዋጉ!” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ በርቱ ወንድነታችሁም ይታይ፤ አለዚያ ባሪያ እንዳደረጋችኋቸው ሁሉ፣ ዕብራውያን እናንተን መልሰው ባሪያ ያደርጓችኋል። ወንድነታችሁ ይታይ፤ ተዋጉ!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ በርቱ! ወንድነታችሁም ይታይ፤ ያለዚያ ባርያ እንዳደረጋችኋቸው ሁሉ፥ ዕብራውያን እናንተን መልሰው ባርያ ያደርጓችኋል። ስለዚህ በወንድነት ጠንክራችሁ ተዋጉ!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ፍልስጥኤማውያን ሆይ! በርቱ፤ ጐብዙ፤ እናንተ ባሪያዎች እንዳደረጋችኋቸው ዕብራውያን ባሪያዎች እንዳያደርጓችሁ በርቱ፤ ተዋጉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ፍልስጥኤማውያን ሆይ፥ አይዞአችሁ፥ ጎብዙ፥ እናንተ ባሪያዎች እንዳደረጋችኋቸው ዕብራውያን ባሪያዎች እንዳያደርጉአችሁ ጎብዙ፥ ተዋጉ። |
እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል በርትተን እንዋጋ! እንግዲህ ሁሉ ነገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!”
የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል።
አንተ ማንም ጥፋት ሳያደርስብህ ጥፋተኛ የሆንክ! ማንም ሳይከዳህ ከዳተኛ የሆንክ ወዮልህ! ጥፋትን ማድረስህን ስታቆም ትጠፋለህ፤ ከዳተኛነትህንም ስታቆም ክዳት ይደርስብሃል።
ከፍልስጥኤማውያን ጋር በመተባበር ወደ ጦሩ ሰፈር ሄደው የነበሩ አንዳንድ ዕብራውያንም ፍልስጥኤማውያንን ከድተው ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ተባበሩ።