1 ሳሙኤል 4:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥላም “የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በመማረኩ ምክንያት የእግዚአብሔር ክብር ከእስራኤል ተለየ” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ “የእግዚአብሔር ታቦት ተማርኳልና ክብር ከእስራኤል ተለይቷል” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም፥ “የእግዚአብሔር ታቦት ተማርኳልና ክብር ከእስራኤል ተለይቶአል” አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “የእግዚአብሔር ታቦት ተማርካለችና ክብር ከእስራኤል ለቀቀ” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም፦ የእግዚአብሔር ታቦት ተማርካለችና ክብር ከእስራኤል ለቀቀ አለች። |
እግዚአብሔር በቊጣው ጽዮንን ምንኛ አዋረዳት! ወደ ሰማይ ከፍ ብላ የነበረችውን የእስራኤልን መመኪያ ወደ ምድር ጣላት፤ በቊጣው ቀን የእግሩ ማሳረፊያ መሆንዋን ሊያስታውስ አልፈቀደም።
በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ አስቀድሜ የተናገርኩትን ብርቱ የማስጠንቀቂያ ቃል ሁሉ በተግባር እፈጽማለሁ፤