1 ሳሙኤል 4:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወሬ ነጋሪው የቃል ኪዳኑን ታቦት መማረክ ባወሳ ጊዜ ዔሊ በቅጽሩ በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ተገልብጦ ወደ ኋላው ወደቀ፤ እርሱም ሽማግሌ ከመሆኑም በላይ በውፍረቱ ግዙፍ ስለ ነበር ከአወዳደቁ የተነሣ አንገቱ ተሰብሮ ሞተ፤ ዔሊም በእስራኤል መሪ ሆኖ የቈየበት ዘመን አርባ ዓመት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየው ስለ እግዚአብሔር ታቦት በተናገረ ጊዜ፣ ዔሊ በቅጥሩ በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ በጀርባው ወደቀ፤ እርሱም ያረጀና ሰውነቱም የሚከብድ ስለ ነበር፣ ዐንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱም ለአርባ ዓመት በእስራኤል ላይ ፈራጅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውየው ስለ እግዚአብሔር ታቦት በተናገረ ጊዜ፥ ዔሊ በቅጥሩ በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ በጀርባው ወደቀ፤ እርሱም ያረጀና ሰውነቱም የሚከብድ ስለ ነበር፥ ዐንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱ ለአርባ ዓመት በእስራኤል ላይ ፈራጅ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርንም ታቦት ባሰባት ጊዜ በበሩ አጠገብ ካለው ከወንበሩ ወደቀ፤ እርሱ ሸምግሎ፥ ደንግዞም ነበርና ጀርባው ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውዮውም ስለ እግዚአብሔር ታቦት በተናገረ ጊዜ ዔሊ በበሩ አጠገብ ካለው ከወንበሩ ወደቀ፥ እርሱ ሸምግሎ ደንግዞም ነበርና አንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት ፈራጅ ነበረ። |
ሙሴም አሮንን “እግዚአብሔር ‘በፊቴ ቀርቦ የሚያገለግለኝ ሁሉ ቅድስናዬን ያክብር፤ እኔም በሕዝቤ ፊት የተከበርኩ እሆናለሁ’ እያለ በተናገረበት ጊዜ ይህንኑ ማስጠንቀቁ ነበር” አለው። አሮንም መልስ ሳይሰጥ ዝም አለ።
ሰውዬው በደረሰ ጊዜ ልቡ ለእግዚአብሔር ታቦት ተጨንቆ የነበረው ዔሊ በመንገድ ዳር በወንበር ተቀምጦ ይመለከት ነበር። ሰውዬውም ወደ ከተማ መጥቶ ወሬውን በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ከፍተኛ ጩኸት አስተጋቡ።
ወሬ ነጋሪውም “እስራኤላውያን ድል ሆነው ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ይህም ሽንፈት በእኛ ላይ መድረሱ እጅግ አሠቃቂ ነው፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ፤ የእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ተማረከች” ሲል መለሰለት።
የፊንሐስ ሚስት የነበረችው የዔሊ ምራት ነፍሰ ጡር ነበረች፤ የምትወልድበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት መማረኩን፤ ዐማትዋና ባልዋ መሞታቸውን በሰማች ጊዜ በድንገተኛ ምጥ ተይዛ ወለደች፤ ምጡም ጸንቶባት ነበር፤