1 ሳሙኤል 4:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወሬ ነጋሪውም “እስራኤላውያን ድል ሆነው ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ይህም ሽንፈት በእኛ ላይ መድረሱ እጅግ አሠቃቂ ነው፤ ከዚህም ሁሉ ጋር ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ተገደሉ፤ የእግዚአብሔርም የቃል ኪዳን ታቦት ተማረከች” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወሬውን ያመጣውም ሰው፣ “እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ሰራዊቱም ከፍተኛ ዕልቂት ደርሶበታል፤ እንዲሁም ሁለቱ ልጆችህ አፍኒንና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት ተማርኳል” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወሬውን ያመጣውም ሰው፥ “እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ሠራዊቱም ከፍተኛ እልቂት ደርሶበታል፤ እንዲሁም ሁለቱ ልጆችህ ሖፍኒና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት ተማርኳል” ብሎ መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ሰው መልሶ፥ “እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ደግሞም በሕዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖአል፥ ሁለቱም ልጆችህ አፍኒንና ፊንሐስ ሞተዋል፤ የእግዚአብሔርም ታቦት ተማርካለች” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወሬኛውም መልሶ፦ እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ ደግሞ በሕዝቡ ዘንድ ታላቅ ግድያ ሆኖአል፥ ሁለቱም ልጆችህ አፍኒንና ፊንሐስ ሞተዋል፥ የእግዚአብሔርም ታቦት ተማርካለች አለ። |
እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦ “እነሆ እኔ በእስራኤል ላይ አንድ ነገር የማደርግበት ቀን ተቃርቦአል፤ ያን ነገር በጆሮው የሚሰማው ሁሉ ይዘገንነዋል።
በዚያም ቀን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ በዔሊና በቤተሰቡ ላይ አስቀድሜ የተናገርኩትን ብርቱ የማስጠንቀቂያ ቃል ሁሉ በተግባር እፈጽማለሁ፤
ሰውየውም ቀርቦ “እኔ ከጦርነቱ አምልጬ መጣሁ፤ ዛሬም እዚህ የደረስኩት በብርቱ ሩጫ ነው” አለ። ዔሊም “ልጄ ሆይ! ታዲያ እንዴት ሆነ?” አለው።
ወሬ ነጋሪው የቃል ኪዳኑን ታቦት መማረክ ባወሳ ጊዜ ዔሊ በቅጽሩ በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ተገልብጦ ወደ ኋላው ወደቀ፤ እርሱም ሽማግሌ ከመሆኑም በላይ በውፍረቱ ግዙፍ ስለ ነበር ከአወዳደቁ የተነሣ አንገቱ ተሰብሮ ሞተ፤ ዔሊም በእስራኤል መሪ ሆኖ የቈየበት ዘመን አርባ ዓመት ነበር።