ባለሟሎቹ ሁሉ በእርሱ በኩል አለፉ፤ የዳዊት ክብር ዘበኞች የነበሩት ከሪታውያንና ፈሊታውያን፥ እንዲሁም ከጋት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያን በንጉሡ ፊት አለፉ፤
1 ሳሙኤል 30:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ተከታዮቹ ወጥተው ሄዱ፤ ብሦር ተብሎ በሚጠራው ወንዝ አጠገብ በደረሱ ጊዜ፥ ጥቂቶቹ በዚያ ዕረፍት በማድረግ ቈዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊትና ዐብረውት የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ወደ ቦሦር ወንዝ መጡ፤ ጥቂቶቹም በቦሦር ወንዝ ቈዩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዳዊትና አብረውት የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ብሦር ተብሎ ከሚጠራው ወንዝ ሲደርሱ፤ ጥቂቶቹ በብሦር ወንዝ ቆዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከእርሱም ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ሄዱ፤ እስከ ቦሦር ወንዝ ድረስም መጡ፤ ከእነርሱም የቀሩት በዚያ ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ከእርሱም ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ሄዱ፥ እስከ ቦሦር ወንዝ ድረስም መጡ፥ ከእነርሱም የቀሩት በዚያ ተቀመጡ። |
ባለሟሎቹ ሁሉ በእርሱ በኩል አለፉ፤ የዳዊት ክብር ዘበኞች የነበሩት ከሪታውያንና ፈሊታውያን፥ እንዲሁም ከጋት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያን በንጉሡ ፊት አለፉ፤