ስለዚህ ዳዊት ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋር ወደ ኬብሮን ሄደ፤ እነርሱም የኢይዝራኤል ተወላጅ የሆነችው የአሒኖዓምና የቀርሜሎሳዊው የሟቹ የናባል ሚስት አቢጌል ነበሩ።
1 ሳሙኤል 30:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች የኢዝራኤላይቱን አሒኖዓምና የቀርሜሎሳይቱ የናባል ሚስት የነበረችው አቢጌል ተማርከው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች ማለትም ኢይዝራኤላዊቷ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢግያም ተማርከው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች ማለትም ኢይዝራኤላዊቷ አሒኖዓምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢጌልም ተማርከው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትም ሁለቱ ሚስቶቹ ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቤግያ ተማርከው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም ሁለቱ ሚስቶቹ ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢግያ ተማርከው ነበር። |
ስለዚህ ዳዊት ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋር ወደ ኬብሮን ሄደ፤ እነርሱም የኢይዝራኤል ተወላጅ የሆነችው የአሒኖዓምና የቀርሜሎሳዊው የሟቹ የናባል ሚስት አቢጌል ነበሩ።
ዳዊትና ተከታዮቹም ከቤተሰቦቻቸው ጋር በጋት ተቀመጡ፤ ከዳዊትም ጋር ሁለቱ ሚስቶቹ አብረው ነበሩ፤ እነርሱም የኢይዝራኤል ተወላጅ የሆነችው አሒኖዓምና የቀርሜሎሱ ተወላጅ ናባል አግብቶአት የነበረው አቢጌል ነበሩ፤