1 ሳሙኤል 30:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሰጠን ድል እናንተ ይህን ማድረግ አትችሉም! እኛን በሕይወት ጠብቆ በወራሪዎች ላይ ድልን የሰጠን እርሱ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ወንድሞቼ ሆይ፤ የጠበቀን፣ የመጣብንንም ወራሪ በእጃችን የጣለልን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በሰጠን ነገር ይህን ማድረግ አይገባችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼ ሆይ፤ የጠበቀን፥ የመጣብንንም ወራሪ በእጃችን የጣለልን ጌታ ነው፤ እርሱ በሰጠን ነገር አስተውሉ፤ ይህን ማድረግ አይገባችሁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም አለ፥ “እግዚአብሔር አሳልፎ ከሰጠን በኋላ እንዲህ አታድርጉ፤ እርሱ ጠብቆናል፤ በእኛም ላይ የመጡትን ሠራዊት በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ የጠበቀን በእኛም ላይ የመጣውን ጭፍራ በእጃችን አሳልፎ የሰጠን እግዚእብሔር በሰጠን ነገር እንዲህ አታድርጉ፥ |
እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞቼና አባቶቼ ሆይ! እስቲ ስሙኝ! አባታችን አብርሃም በካራን ለመኖር ከመሄዱ በፊት ገና በመስጴጦምያ ሳለ የክብር አምላክ ተገለጠለትና
ባለጸጋ እንድትሆን ኀይልና ብርታት የሰጠህ እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ እርሱ ይህን የሚያደርግበት ምክንያት ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።
ሽማግሌው ግን ወደ ውጪ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “አይሆንም ወዳጆቼ ሆይ! እባካችሁ ይህን የመሰለ አስከፊ ነገር አታድርጉ! ይህ ሰው የእኔ እንግዳ ነው፤
ነገር ግን ከዳዊት ጋር አብረው ከሄዱት መካከል የብልግና ጠባይ ያለባቸው አንዳንድ የማይረቡ ሰዎች “ከእኛ ጋር ወደ ጦርነቱ ስላልሄዱ ምርኮ ልናካፍላቸው አይገባም፤ ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን ብቻ ተረክበው ወዲያ ይሂዱ” አሉ።
እናንተ በምትሉት ነገር ማንም አይስማማበትም! ወደ ኋላ ቀርቶ ጓዝ ሲጠብቅ የቈየውም ሆነ ወደ ጦርነት የዘመተው ሁሉም የተገኘውን ምርኮ እኩል መካፈል አለበት” ሲል መለሰላቸው።
ዳዊትም “እነዚያን ወራሪዎች ተከታትዬ በማሳደድ ልያዛቸውን?” ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “ተከተላቸው! እነርሱንም ይዘህ ምርኮኞችን በመታደግ ታድናለህ” ሲል መለሰለት።