1 ሳሙኤል 30:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ግን ከአራት መቶ ተከታዮቹ ጋር ማሳደዱን ቀጠለ፤ ሌሎቹ ሁለት መቶ ተከታዮቹ ግን ወንዙን ለመሻገር ስለ ደከሙ ወደ ኋላ ቀሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት መቶዎቹ እጅግ ዝለው ስለ ነበር ወንዙን መሻገር አልቻሉምና። ነገር ግን ዳዊትና አራት መቶ ሰዎች መከታተላቸውን ቀጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት መቶዎቹ እጅግ ዝለው ስለ ነበር ወንዙን መሻገር አልቻሉም። ነገር ግን ዳዊትና አራት መቶ ሰዎች መከታተላቸውን ቀጠሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከእርሱም ጋር ያሉት አራት መቶ ሰዎች አሳደዱ፤ ሁለቱ መቶ ሰዎች ግን የቦሦር ወንዝን መሻገር ደክመዋልና በኋላ ቀሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ከእርሱም ጋር ያሉት አራት መቶ ሰዎች አሳደዱ፥ ሁለቱ መቶ ሰዎች ግን የቦሦር ወንዝን መሻገር ደክመዋልና በኋላ ቀሩ። |
ከዚህ በኋላ ሳኦልና ወታደሮቹ ካሉበት በመንቀሳቀስ ወደ ውጊያው ሄዱ፦ እዚያም ፍልስጥኤማውያን ግራ በመጋባት እርስ በርሳቸው በሰይፍ ይጋደሉ ነበር።
በዚያን ቀን እስራኤላውያን ከሚክማስ እስከ አያሎን ባለው መንገድ ሁሉ እያሳደዱ በመውጋት ፍልስጥኤማውያንን ድል መቱ፤ በዚህም ጊዜ እስራኤላውያንም በራብ እጅግ ዝለው ነበር።
ዳዊትም ደክሞአቸው በብሦር ምንጭ አጠገብ ዕረፍት በማድረግ ቈይተው ወደነበሩት ወደ ሁለት መቶ ተከታዮቹ ተመልሶ ሄደ። እነርሱም ዳዊትንና ተከታዮቹን ሊቀበሉአቸው መጡ፤ ዳዊትም ወደ እነርሱ ቀረብ ብሎ ደኅንነታቸውን በመጠየቅ ሰላምታ አቀረበላቸው።
ስለዚህም ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ተከታዮቹ ወጥተው ሄዱ፤ ብሦር ተብሎ በሚጠራው ወንዝ አጠገብ በደረሱ ጊዜ፥ ጥቂቶቹ በዚያ ዕረፍት በማድረግ ቈዩ።