እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን ቃል ልስማ፤ እንደገና በስሕተት መንገድ ካልሄዱ በቀር፥ ለሕዝቡና ለታማኞቹ ሰላምን እንደሚሰጥ ተስፋ ሰጥቶአል።
1 ሳሙኤል 3:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም “ወደ መኝታህ ተመልሰህ ሂድ፤ እንደገናም የጠራህ እንደ ሆነ ‘ጌታ ሆይ፥ እነሆ እኔ አገልጋይህ እሰማለሁና ተናገር’ በለው” ሲል ሳሙኤልን መከረው። ሳሙኤልም ተመልሶ ወደ መኝታው ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ዔሊ ሳሙኤልን፣ “ሂድና ተኛ፤ ከእንግዲህ ቢጠራህ ግን፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር’ በል” አለው። ስለዚህም ሳሙኤል ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ዔሊ ሳሙኤልን፥ “ሂድና ተኛ፤ ከእንግዲህ ቢጠራህ ግን፥ ‘ጌታ ሆይ፤ አገልጋይህ ይሰማልና ተናገር’ በል” አለው። ሳሙኤልም ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሊም ሳሙኤልን፥ “ልጄ፥ ሄደህ ተኛ፤ ቢጠራህም፦ አቤቱ፥ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር በለው፥” አለው። ሳሙኤልም ሄዶ በስፍራው ተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሊም ሳሙኤልን፦ ሄደህ ተኛ፥ ቢጠራህም፦ አቤቱ፥ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር በለው አለው። ሳሙኤልም ሄዶ በስፍራው ተኛ። |
እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን ቃል ልስማ፤ እንደገና በስሕተት መንገድ ካልሄዱ በቀር፥ ለሕዝቡና ለታማኞቹ ሰላምን እንደሚሰጥ ተስፋ ሰጥቶአል።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር “ማንን እልካለሁ? መልእክተኛ የሚሆንልንስ ማን ነው?” ሲል ሰማሁት፤ እኔም “እነሆ እኔ እሄዳለሁ! እኔን ላከኝ!” አልኩ።
እርሱም “አንተ በእግዚአብሔር ዘንድ የተወደድክ ሰው ሆይ! መልካም ይሆንልሃል፤ አትፍራ! አይዞህ በርታ!” አለኝ። እርሱም በተናገረኝ ጊዜ ብርታት አገኘሁና “ጌታዬ ሆይ፥ ብርታት ስለ ሰጠኸኝ እነሆ፥ ተናገር” አልኩት።
ጐልማሳውም “የእናንተም ሆነ የጠላት ወገን አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አዛዥ እንደ መሆኔ መጠን እነሆ፥ መጥቻለሁ” አለ። ኢያሱም ወደ መሬት ወድቆ ሰገደለትና “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገልጋይህ ምን ልታዘዝ?” አለው።
እግዚአብሔርም መጥቶ በዚያ ቆመ፤ ከዚያም በፊት ያደርግ በነበረው ዐይነት “ሳሙኤል! ሳሙኤል!” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም “ጌታ ሆይ! እነሆ አገልጋይህ እሰማለሁና ተናገር” አለው።
እግዚአብሔርም እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ሳሙኤልን ጠራው፤ ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ ዔሊ በመሄድ “እነሆ! ስለጠራኸኝ መጥቻለሁ” አለው። ከዚህም በኋላ ሳሙኤልን ይጠራው የነበረው እግዚአብሔር መሆኑን ዔሊ ተገነዘበ፤