La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 3:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም የተነሣ በሀገሪቱ ዳር እስከ ዳር የሚኖሩ እስራኤላውያን ሁሉ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑን ዐወቁ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል በርግጥ የእግዚአብሔር ነቢይ መሆኑን ዐወቁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉ እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል የታመነ የጌታ ነቢይ መሆኑን ዐወቁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከዳን እስከ ቤር​ሳ​ቤህ ድረስ ሳሙ​ኤል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ ይሆን ዘንድ የታ​መነ እንደ ሆነ ዐወቀ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እስራኤልም ሁሉ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሳሙኤል ለእግዚአብሔር ነቢይ ይሆን ዘንድ የታመነ እንደ ሆነ አወቀ።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 3:20
10 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ እኔ የምመክርህ፥ ከአገሪቱ አራት ማእዘኖች ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉትንና ብዛታቸው እንደ ባሕር ዳር አሸዋ የሆነው እስራኤላውያን ሁሉ በአንድነት ሰብስበህ አንተው ራስህ አዛዥ በመሆን ወደ ጦርነቱ እንድትመራቸው ነው።


በኖረበትም ዘመን ሁሉ ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ መላው የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ ያለስጋት በሰላም ይኖር ነበር፤ እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ የሆነ የወይን ተክልና የበለስ ዛፍ ስለ ነበረው በእነዚህ ተክሎች ጥላ ሥር ያርፍ ነበር።


ነገር ግን አንተ የተናገርካቸው ቃላት በእርግጥ ይፈጽማሉ፤ እውን ሆነው በሚፈጸሙበትም ጊዜ በመካከላቸው ነቢይ መኖሩን ያውቃሉ።”


ከወንዶች ልጆቻችሁ መካከል አንዳንዶቹን ነቢያት፥ ከወጣቶቻችሁም መካከል አንዳንዶቹን ናዝራውያን አድርጌ አስነሣሁላችሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ታዲያ ይህ እውነት አይደለምን? እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።


ከዚህም በኋላ ለአራት መቶ ኀምሳ ዓመት ያኽል እስከ ነቢዩ ሳሙኤል ድረስ መሳፍንትን ሰጣቸው።


“ ‘አንድ ነቢይ የሚናገረው የትንቢት ቃል ከእግዚአብሔር ያልተሰጠ መሆኑን በምን ለይቼ ዐውቃለሁ?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።


እኔን ለአገልግሎት በመሾም ታማኝ አድርጎ የቈጠረኝንና የሰጠኝን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰግናለሁ።


ከሰሜን እስከ ደቡብ፥ ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ እንዲሁም በስተምሥራቅ በገለዓድ ምድር ያሉት የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ለጦርነት ተዘጋጁ፤ በአንድነትም ሆነው በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት ተሰበሰቡ፤


እግዚአብሔርም መጀመሪያ ጌዴዎንን፥ ከዚያም በኋላ ባራቅንና ዮፍታሔን፥ ከዚያም ሶምሶንን፥ በመጨረሻም እኔን ላከ፤ እኛም እያንዳንዳችን እናንተን ከጠላቶቻችሁ አዳናችሁ፤ በሰላምም ኖራችሁ፤