ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼአለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤
1 ሳሙኤል 28:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ደግሞ አሁን የእኔን የአገልጋይህን ቃል ስማ፤ ምግብ ላዘጋጅልህና ተመገብ መንገድህንም በርትተህ መሄድ ትችላለህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እባክህ አገልጋይህ የምትልህን ስማ፤ ብርታት አግኝተህ መሄድ እንድትችል፣ ጥቂት ምግብ ላቅርብልህና ብላ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እባክህ አገልጋይህ የምትልህን ስማ፤ ብርታት አግኝተህ መሄድ እንድትችል፥ ጥቂት ምግብ ላቅርብልህና ብላ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን እንግዲህ አንተ ደግሞ የአገልጋይህን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ፤ በፊትህም ቁራሽ እንጀራ ላኑርልህ፤ መንገድም ትሄዳለህና ትበረታ ዘንድ ብላ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን እንግዲህ አንተ ደግሞ የባሪያህን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ፥ በፊትህም ቁራሽ እንጀራ ላኑርልህ በመንገድም ስትሄድ ትበረታ ዘንድ ብላ አለችው። |
ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼአለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤
ሳኦል “ምንም ነገር አልቀምስም” ብሎ እምቢ አለ፤ ይሁን እንጂ ባለሟሎቹም እንዲመገብ አበረታቱት፤ በመጨረሻም “እሺ” ብሎ ከወደቀበት መሬት በመነሣት አልጋ ላይ ተቀመጠ፤