እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደ ተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች።
1 ሳሙኤል 26:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል በሐኪላ ተራራ ላይ በሚገኘው መንገድ አጠገብ በሔሲሞን ፊት ለፊት ሰፈረ፤ ዳዊትም በምድረ በዳ ነበር፤ ሳኦል እርሱን ለመፈለግ መምጣቱን ባየ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም በየሴሞን ትይዩ በሚገኘው በኤኬላ ኰረብታ ላይ በመንገድ ዳር ሰፈረ፤ ዳዊት ግን በምድረ በዳ ነበር። ዳዊትም ሳኦል እዚያ ድረስ እንደ ተከተለው ባወቀ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም በየሴሞን ትይዩ በሚገኘው በሐኪላ ኰረብታ ላይ በመንገድ ዳር ሰፈረ፤ ዳዊት ግን በምድረ በዳ ነበር። ዳዊትም ሳኦል እዚያ ድረስ እንደ ተከተለው ባወቀ ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ በመንገዱ አጠገብ ሰፈረ። ዳዊትም በምድረ በዳ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፥ ዳዊትም ሳኦል ሊፈልገው ወደ ምድረ በዳ እንደ መጣ ዐወቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ በመንገዱ አጠገብ ሰፈረ። ዳዊትም በምድረ በዳ ውስጥ ተቀምጦ ነበር፥ ሳኦልም በስተ ኋላው ወደ ምድረ በዳ እንደ መጣ አየ። |
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደ ተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች።
ከዚፍ ነዋሪዎች አንዳንዶቹ በጊብዓ ወደሚገኘው ወደ ሳኦል ሄደው እንዲህ አሉ፥ “ዳዊት በእኛ ግዛት ውስጥ ከይሁዳ ምድረ በዳ በስተ ደቡብ ባለው በሐኪላ ተራራ ላይ በምትገኘው በሖሬሽ ተሸሽጎ ይገኛል።
በመንገድ ዳር ባሉት የበጎች ማደሪያዎች አቅራቢያ ወደሚገኘው ወደ አንድ ዋሻ ወገቡን ሊሞክር ወደ ውስጥ ገባ፤ በዚያም እርሱ ከተቀመጠበት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ዳዊትና ተከታዮቹ ተደብቀው የሚኖሩበት ክፍል ነበር፤
ጥቂት ሰዎች ከዚፍ ተነሥተው ሳኦል ወዳለበት ወደ ጊብዓ በመምጣት “እነሆ፥ ዳዊት ከይሁዳ ምድረ በዳ ዳርቻ በተለይ ሐኪላ ተብሎ በሚጠራው ተራራ ላይ ተደብቆ ይገኛል” ብለው ነገሩት፤