እርሱም የልጁ ልብስ መሆኑን ተረድቶ “በእርግጥ የእርሱ ልብስ ነው! አንድ ክፉ አውሬ ገድሎታል፤ ልጄን ዮሴፍን አውሬ ቦጫጭቆ በልቶታል!” አለ።
1 ሳሙኤል 26:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም የዳዊትን ድምፅ ለይቶ ስላወቀ “ዳዊት ልጄ ሆይ! በእርግጥ ይህ ቃል የአንተ ነውን?” ሲል ጠየቀ። ዳዊትም “አዎ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ድምፄ ነው ሲል መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል የዳዊትን ድምፅ ለይቶ ስላወቀ፣ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ ይህ ድምፅህ ነውን?” አለው። ዳዊትም፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ አዎን ድምፄ ነው” ሲል መለሰ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል የዳዊትን ድምፅ ለይቶ ስላወቀ፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ፤ በእርግጥ የአንተ ድምፅ ነውን?” አለው። ዳዊትም፥ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ አዎን ድምፄ ነው” ሲል መለሰ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም የዳዊት ድምፅ እንደ ሆነ ዐውቆ፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድምፅህ ነውን?” አለው። ዳዊትም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! አዎ እኔ ባሪያህ ነኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም የዳዊት ድምፅ እንደ ሆነ አውቆ፦ ልጄ ዳዊት ሆይ፥ ይህ ድምፅህ ነውን? አለው። ዳዊትም፦ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ድምፄ ነው አለው። |
እርሱም የልጁ ልብስ መሆኑን ተረድቶ “በእርግጥ የእርሱ ልብስ ነው! አንድ ክፉ አውሬ ገድሎታል፤ ልጄን ዮሴፍን አውሬ ቦጫጭቆ በልቶታል!” አለ።
ከዚያም በኋላ ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “አንተ እውነተኛ ሰው ነህ! እኔ ግን ስሕተተኛ ነኝ፤ ይህን የመሰለ በደል ስፈጽምብህ አንተ ለእኔ ቸርነት አድርገህልኛል!
ዳዊትም ከዚያ ወጥቶ ሳኦልን በመከተል “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ!” አለው፤ ሳኦልም መለስ ብሎ ዙሪያውን ሲመለከት ዳዊት በመሬት ላይ ለጥ ብሎ እጅ ነሣውና እንዲህ አለው፤