1 ሳሙኤል 26:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድምፁንም ከፍ አድርጎ ወደ ሳኦል ወታደሮችና ወደ አበኔር በመጮኽ “አበኔር ሆይ! መልስ ስጠኝ” አለው። አበኔርም “እንዲህ እያልክ በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ሰራዊቱንና የኔርን ልጅ አብኔርን፣ “አበኔር ሆይ፣ አትመልስልኝምን?” ሲል ተጣራ። አበኔርም፣ “በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” በማለት መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ሠራዊቱንና የኔርን ልጅ አቤኔርን፥ “አቤኔር ሆይ፥ አትመልስልኝምን?” ሲል ተጣራ። አቤኔርም፥ “በንጉሡ ላይ የምትጮኽ አንተ ማነህ?” በማለት መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሕዝቡንና የኔር ልጅ አቤኔርን ጠራቸው፥ “አቤኔር ሆይ፥ አትመልስምን?” አለው። አቤኔርም መልሶ፥ “አንተ የምትጠራኝ ማን ነህ?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ለሕዝቡና ለኔር ልጅ ለአበኔር፦ አበኔር ሆይ፥ አትመልስምን? ብሎ ጮኸ። አበኔርም መልሶ፦ ለንጉሡ የምትጮኸው አንተ ማን ነህ? አለ። |
ዳዊትም “አበኔር! አንተ በእስራኤል የታወቅህ ታላቅ ሰው አይደለህምን? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን በደንብ የማትጠብቀው ስለምንድን ነው? እነሆ፥ ከእኛ አንድ ሰው ጌታህን ለመግደል ወደ ሰፈር ገብቶ ነበር፤