1 ሳሙኤል 26:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥቂት ሰዎች ከዚፍ ተነሥተው ሳኦል ወዳለበት ወደ ጊብዓ በመምጣት “እነሆ፥ ዳዊት ከይሁዳ ምድረ በዳ ዳርቻ በተለይ ሐኪላ ተብሎ በሚጠራው ተራራ ላይ ተደብቆ ይገኛል” ብለው ነገሩት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዚፍ ሰዎች ሳኦል ወዳለበት ወደ ጊብዓ መጥተው፣ “እነሆ፤ ዳዊት በየሴሞን ትይዩ በሚገኘው በኤኬላ ኰረብታ ተደብቋል” ብለው ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚፍ ሰዎችም ወደ ጊብዓ ወደ ሳኦል መጥተው፦ “እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በሐኪላ ኮረብታ ላይ ተሸሽጓል” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚፍ ሰዎችም ከአውክሞዲስ ወደ ኮረብታው ወደ ሳኦል መጥተው፥ “እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ ከእኛ ጋር ተሸሽጎ አለ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዚፍ ሰዎችም ወደ ጊብዓ ወደ ሳኦል መጥተው፦ እነሆ፥ ዳዊት በየሴሞን ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ ተሸሽጎአል አሉት። |
ከዚፍ ነዋሪዎች አንዳንዶቹ በጊብዓ ወደሚገኘው ወደ ሳኦል ሄደው እንዲህ አሉ፥ “ዳዊት በእኛ ግዛት ውስጥ ከይሁዳ ምድረ በዳ በስተ ደቡብ ባለው በሐኪላ ተራራ ላይ በምትገኘው በሖሬሽ ተሸሽጎ ይገኛል።
ሳኦል በሐኪላ ተራራ ላይ በሚገኘው መንገድ አጠገብ በሔሲሞን ፊት ለፊት ሰፈረ፤ ዳዊትም በምድረ በዳ ነበር፤ ሳኦል እርሱን ለመፈለግ መምጣቱን ባየ ጊዜ፥